loading
በድሬዳዋ ከተማ ከትናንት ጠዋት ጀምሮ በተከሰተው ግጭት የአሥር ሰዎች ህይወት ማለፉን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን እና ንብረት መውደሙን ፖሊስስ ገለፀ፡፡

ግጭቱ በተከሰተበት ቀበሌ 09 እና አካባቢው በአሁኑ ሰዓት የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ለአርትስ ቲቪ አስታውቋል፡፡ የሰዎች ህይወት ያለፈው ከእሳት ቃጠሎ ጋር በተገናኘ እንደሆነ የገለፀው ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር እያዋልኩ ነው ብሏል፡፡ የሰላም ተምሳሌቷ ድሬ ወደቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ ወጣቶችና የአገር ሽማግሌዎች አሁንም እየሰሩ እንደሆነ የገለፁልን ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ […]

የሶማሌ ክልል አዲሱ ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ መሀመድ የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሀመድ ኦማር ስልጣን እንዳስረከቡና ሽግግሩም በሰላም እንደተጠናቀቀ ለቢቢሲ ሶማልኛ ተናግረዋል።

የክልሉ አዲሱ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ስልጣን ለመልቀቅ በመጠየቃቸው የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አዲሱን የክልሉ ፕሬዚዳንት እንደመረጠም ገልፀዋል። ሰሞኑን ከብዙ ሰዎች ሞት፣ አብያተ ክርስትያናት መቃጠልና ንብረት መውደም ጋር ተያይዞም በክልሉ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን በክልሉ ከነበረው አለመረጋጋትና ተቃውሞዎች ጋር ተያይዞም በማዕከላዊ መንግሥት ግፊት ምክንያት አብዲ ኢሌ ከስልጣን እንደወረዱ ብዙዎች አስተያታቸውን ቢሰጡም አዲሱ ፕሬዚዳንት ሲንከባለል […]

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት በደረሰዉ የሰዉ ህይወት መጥፋትና ንብረት መዉደም ማዘንዋን ገለጸች፡፡

ቤተክርስትያንዋ ሀዘንዋን የገለጸችዉ ዛሬ የተጀመረዉን የፍልሰታን ጾም አስመልክቶ ለአርትስ ቲቪ በላከችዉ መግለጫ ነዉ፡፡ በመግለጫዉ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀጳጳስ ካርዲናል ብርሃነየሱስ እንዳስታወቁት የፍልሰታ ጾም የተጀመረዉ ቤተክርስትያናችን 19ነኛዉን የአመሰያን ጉባኤ በስኬት ባስተናገደች ማግስት በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል፡፡ ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተዉ ግጭት ምክንያት የሰዉ ህይወት በማለፉ ሀዘን ተሰምቶናል፡፡ቤተክርስትያንዋም ለሰላም ትጸልያለች ብለዋል፡፡ ካርዲናሉ በመግለጫቸዉ በአሁኑ ወቅት ምእመናንም በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉና […]

አብዲ ሞሃመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አብዲ ሞሃመድ ዑመር ትናንት ከክልሉ ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ቢገለጽም የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ ተብሎ ነበር። የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት በመከላከያ ሠራዊት አባላት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉ በኋላ ጅግጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግሥት እንደተወሰዱ ምንጮች ለቢቢሲ ሶማልኛ ገልጸዋል። ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በክልሉ ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ […]

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያውን ወደ “ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ ማቅረቡ ተገለፀ።

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያውን ወደ “ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ለመቀየር ሀሳብ ማቅረቡ ተገለፀ። የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት፥ የኦህዴድን የስያሜ እና የአርማ ለውጥ ለማድረግ ሀሳብ ቀርቧል። በዚህም መሰረት አዲሱ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ መጠሪያ “የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” እንዲሆን ሀሳብ መቅረቡን ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት። ከዚህ በተጨማሪም ኦህዴድ ከዚህ […]

ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተዉጣጡ የህክምና ባለሞያዎች በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማከም ወደ ጅግጅጋ አቀኑ፡፡

ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተዉጣጡ የህክምና ባለሞያዎች በጅግጅጋ በተከሰተዉ ግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማከም ወደ ጅግጅጋ አቀኑ፡፡ ሀኪሞቹ ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ከየካቲት12 እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኔየም ሜዲካል ኮሌጅ የተወጣጡ መሆናቸዉን የጤና ጥበቃ ምኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በፌስቡክ ገጻቸዉ ገልጸዋል ወደ ጂግጂጋ የተጓዙት የጤና ባለሞያዎች ሃያ አራት ናቸዉ፡፡

በጂግጂጋ እና ሌሎች ከተሞች የሃገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው የማረጋጋት ስራ መቀጠሉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በጂግጂጋና በሌሎች የሶማሌ ክልል ከተሞች በመግባት የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ላይ ችግሩን በአንድ ጊዜ ለመመለስ ከባድ ቢሆንም መከላከያ ሰራዊት በከተሞች በመግባት ችግር ሲፈጠር መቆጣጠርና ማረጋጋት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉንም ነው የተናገሩት። በስፍራው የተፈጠረውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለማረጋጋት የአካባቢው ነዋሪዎች በተለይም የሃገር ሽማግሌዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል። […]

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ በባሕር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች እና አክቲቪስቶች ጋር በአቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ይወያያል።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጀዋር ሙሃመድ ዛሬ በባሕር ዳር ከሚገኙ ወጣቶች እና አክቲቪስቶች ጋር በአቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ይወያያል። ከጃዋር ጋር ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋቢሳን ጨምሮ ከኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተገኙ ልዑካንም የሚሳተፉ ሲሆን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ አስር ግለሰቦች ከጎንደር እንዲሚገኙ ታውቋል።

የዘንድሮው የሻደይ በዓል ከነሐሴ 16 እስከ 18 በዋግኸምራ ብሔረሰብ ዞን” ሻዴይ በዓላችን ለገጽታ ግንባታችን” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል፡፡

የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ተክሉ ለአርትስ እንደገለጹት በዓሉ በሁሉም ወረዳዎች በጎዳና ላይ ትርኢቶች እና ባህላዊ ክዋኔዎች ይከበራል ፡፡ ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን በሰቆጣ ከተማ የባህል ሲምፖዚየም የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ […]

ዘንድሮ የአሸንዳ በዓል በትግራይ ክልል በድምቀት ይከበራል አለ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ለአርትስ እንደተናገሩት በዓሉን ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡ በዓሉ በዋነኛነት በጎዳና ላይ ትርኢቶች እና ባህላዊ ጭፈራዎች የሚደምቅ ሲሆን የፓናል ውይይት እና የፎቶ አውደርዕይ ፕሮግራሞች ጎን ለጎን እንደሚካሄዱ ኃላፊው ነግረውናል፡፡ በዓሉን ለማክበር የክልሉ ተወላጆች እንዲሁም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ወደ ክልሉ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡