loading
ዛሬ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክያትን በጀዋር መሃመድ የሚመራዉ ቡድን የኦሮሚያ የሚያደርገውን ጉብኝቱን ለጊዜው ማቆሙን ኦ ኤም ኤን ዘገበ።

በዛሬዉ ዕለት በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አስታውቀዋል። አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ነዉ። በአደጋውም እስካሁን የ3 ሰዎች ህይወት […]

አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጥልቅ ግምገማ ማጠናቀቁን ተከትሎ ነው አቶ አህመድ ሽዴ ሊቀ መንበር አድርጎ የመረጠው። የኢሶዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ አህመድ ሽዴን በሙሉ ድምጽ በሊቀ መንበርነት መምረጡም ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ስብሰባው በክልሉ ተፈጥሮ በነበሩው ሁኔታ […]

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ልኡክ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።

በግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ አዳኒ አብዱልቃድር ሄርሞጌ የተመራው እና 3 አባላትን ያለው ልኡኩ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ አቀባበል አድርገዋል። ወደ ሀገር የገባውን ልኡክ የመሩት አቶ አዳኒ አብዱልቃድር ሄርሞጌ፥ ግንባሩ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት የወሰነው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ […]

የህወሀት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን መቐለ በተካሄደው ሰልፍ ባስተላለፉት መልእክት “ያለን አማራጭ ተከባብሮ መኖር አልያም መበታተን” ማለታቸው ትግራይን ለመገንጠል ከሚል የመነጨ ሳይሆን የሀገሪቱ የፌደራል ስርአት እኩልነትን መሰረት ያደረገ መሆኑ ለመጠቆም የተነገረ ነዉ አሉ።

ህወሀት በዚህ ወር 13ኛ ድርጅታዊ ታሪካዊ የለውጥ ጉባኤ ያካሄዳል ተብሏል፡፡ ሊቀመንበሩ በጉባኤው እስካሁን የተደረጉት የለውጥ እንቅስቃሴዎች ወደተግባር ሊለውጥ የሚችል ብቁ አዲስ ትውልድ ወደ አመራርነት ይመጣል ብለዋል። ህወሓት ህገመንግስትን መሰረት አድርጎ ለሚደረግ የለውጥ ጉዞ ደጋፊ እንጂ እንቅፋት እንደማይሆን ዶክተሩ ተናግረዋል። በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት ሊቀመንበሩ ባለፉት አመታት በሀገሪቱ ከተመዘገቡ የልማት ስኬቶች በተጨማሪ በርካታ ጉድለቶች […]

መኢአድ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጠየቀ::

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አገር ለማፍረስ የተቀመጠ ነው ያለውን የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እንዲሰረዝ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ፓርቲውን ይህን ጥያቄ በይፋ ያቀረበው ሐሙስ ነሐሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ‹‹አገር ለማፍረስ የተቀመጠው አንቀጽ 39 የወለደው ችግር የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ይገኛል፤›› በማለት፣ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት መሆኑን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ […]

አቶ ጀዋር መሀመድ በሻሸመኔ የተፈጸመዉን ድርጊት አወገዘ፡፡

በሻሸመኔ ከተማ ለሰዉ ህይወት መጥፋትና የአካል መጉደል ምክንያት የሆኑ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡም በፌስቡክ ገጹ ጠይቋል፡፡ አቶ ጀዋር የሻሸመኔ ህዝብ በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ተቀብሎናል፤ነገርግን በከተማዋ ሊቀበለን የወጣዉ ህዝብ ቁጥር ከተጠበቀዉ በላይ በመሆኑና በህዝቡም መካከል ሀሰተኛ መረጃ በመሰራጨቱ ምክንያት የሰዎች ህይወት አልፏል፤ አካል ጉዳትም ደርስዋል ፤ በዚህም በጣም ማዘኑን ተናግሯል፡፡ ተጨባጭ ባልሆነ መረጃ ንጹህ የሆነ ሰዉን መጉዳት […]

የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘቱን መቀየሩ አሳስቦኛል አለ::

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ፡፡ በባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የጋራ ባህል እሴትዳይሬክተር አቶ አለማየው ጌታቸው የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘት እየተቀየረ መምጣቱንና ስነቃሎቹም ላይ ጥናት ሊደረግ መሆኑን ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ባህል እና ቱሪዝም ቡሄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማደረጉን ገልፀው በመጪው ቡሄ ስነቃላዊ ጥናቶችን ለማድርግ በፌደራል ደረጃ መስሪያ ቤቱ […]

በትግራይ ክልል በመኾኒ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 425 ተቀጣጣይ ፈንጅ ተያዘ።

ተቀጣጣይ ፈንጁ 75 ኪሎ ግራም ክብደት ሲኖረው መኾኒ ከተማ ልዩ ስሙ ገረብ አባ ሃጎስ በተባለ ስፍራ የተያዘ ነው ተብሏል። ፈንጁ ድልድይ ስር ተደብቆ ወደ መቐለ ከተማ ሊሻገር ሲል በህዝቡ ጥቆማ መያዙንም የትግራይ ክልል የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።ፋና እንደዘገበዉ

የቀድሞ የአፋር ክልል ፕሬዝደንት የነበሩት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊ ሚራህ አዲስ አበባ ገቡ፡፡

በሱልጣን ሐንፈሬ አሊ ሚራህ የሚመራውና በስደት በውጭ አገራት ሲኖሩ የነበሩ ልኡካን ቡድን አባላት ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱን ኢብኮ ዘግቧል፡፡ ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ፣ከአፋር ሰብዓዊ መብት አቶ ጋአስ አህመድ እና ከአፋር ነፃ አውጪ ግንባር አቶ ኡመር አሊሚራህ ይገኙበታል፡፡ ልኡካኑ አዲስ አበባ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዲሪ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የአፋር ብሄራዊ […]

ከአዲስ አበባ የተለያዩ የጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች በጅግጅጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 128 ሰዎች የህክምና አገልግሎት ሰጡ፡፡

የህክምና ቡድን መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ትላንት አመሻሽ ላይ ከጅግጂጋ ሲመለሱ በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ቡድኑ በስምንት ቀን ቆይታው ለ128 ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች የህክምና አገልግሎት ድጋፍ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ ከተጎጅዎቹ መካከልም ግማሽ ያህሎቹ የጭንቅላት፣ የደረት፣ የሆድና የደረት ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው መሆኑን ዶ/ር ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ የህክምና ቡድኑ ወደ ጅግጂጋ ከማቅናቱ በፊትም በድሬዳዋ ከተማ […]