ከ12 ከተሞች ተገልጋዮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሚሰጠው አገልግሎት አልረካንም አሉ፡፡
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ከዋልታ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር በመተባበር በከተሞች የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ከተሞች የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ቅንጅታዊ አሰራር ሊከተሉ ይገባል ተብሏል፡፡ ከተሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር እጦት የሰፈነባቸው የምሬት ማዕከል ሆነዋል ያሉት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትር አቶ ጃንጥራር አባይ፤ በአመራሮችና ፈጻሚዎች ድክመት፣ የብቃት ችግር ፣ቀልጣፋና ፍትሃዊ […]