loading
የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ የእስራኤሉ ሞሳድ የስለላ ድርጅት ሀላፊ በደህንነት ዙሪያ ለመወያየት አቡዳቢ ገብተዋል:: ሀላፊው ዮሲ ኮኸን እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዲፕሎማሲ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ አቡዳቢን የጎበኙ የመጀመሪያው ባለ ስልጣን ሆነዋል፡፡ ኮኸን ከኤሜሬቶች የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታኑም ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ሁለቱ ሀገራትበደህንነት እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች […]

አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው:: በሰሜን እና ደቡብ ኮሪያዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ተሟሙቆ የነበረውን አዲስ ግንኙነት ጥላ አጥልቶበታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በድንበር አካባቢ ቀለል ያለ የተኩስ ልውውጥ እስከማድረግ ያደረሳቸው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ሳያንስ ለሽምግልና በሮቻቸውን መዝጋታቸውም ስጋቱን ከፍ አድርጎታል፡፡ ከሴኡል […]

በካሊፎርኒያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ሲያፈናቅል የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተሰምቷል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 14፣ 2012 በካሊፎርኒያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ሲያፈናቅል የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተሰምቷል:: አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በእሳት አደጋው ህይዎቱ ያለፈው ግለሰብ በስራ ላይ የተሰማራ የእሳት አገደጋ ሰራተኛ ነው፡፡ እሳቱ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ በሚሸፍን ቦታ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ማድረሱን የግዛቲቱ ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሰም እንዲህ አይነት የከፋ […]

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በእስራኤል ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 15፣ 2012 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በእስራኤል ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው፡፡የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንዋር ጋርጋሽ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት ወቅት በቴልአቪቭ ኤምባሲያችንን እንከፍታለን ማለታቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ከእስራኤል ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውሰው፤ በዓለም አቀፍ መርህ ሁለት ሀገራት ሊኖራቸው በሚገባው ግንኙነት መሰረት አቡዳቢ በቴላቪቭ ኤምባሲዋን ትከፍታለች ብለዋል፡፡ሚኒስትሩ […]

አሜሪካ በኢራን ላይ በድጋሚ ማዕቀብ ለመጣል ያቀረበችዉን ጥያቄ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዉድቅ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 አሜሪካ በኢራን ላይ በድጋሚ ማዕቀብ ለመጣል ያቀረበችዉን ጥያቄ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዉድቅ አደረገ፡፡ይህንን ተከትሎም አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወሰነዉ ዉሳኔ አሸባሪዎቹን የሚደግፍ ነዉ ብላለች፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታዉ ም/ቤት አባላት አብዛኞቹ የአሜሪካን በድጋሚ ማዕቀብ መጣል መፈለግን እንደተቃወሙትና የም/ቤቱ ፕሬዚዳንት አሜሪካ አሁን ላይ በኢራን ተጨማሪ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ለመጣል የምትችልበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም […]

የኒው ዚላንድ ሙስሊሞችን በጅምላ የጨፈጨፈው ወጣት በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 21፣ 2012 የኒው ዚላንድ ሙስሊሞችን በጅምላ የጨፈጨፈው ወጣት በዕድሜ ልክ እስራት ተቀጣ:: የነጭ የበላይነትን አብዝቶ የሚያቀነቅነው ብሬንተን ታራንት የተባለው የ29 ዓመት ወጣት የፈፀመውን የግድያ ወንጀል ያለ ምንም መከራከሪያ አምኖ ለፍርድ ቤቱ ቃሉን በመስጠቱ ነው ጥፋተኛ የተባለው፡፡ ይህ አውስትራሊያዊ ወጣት ክሪስት ቸርች በተባለ ስፍራ ለፀሎት በተሰባበሱ ሙስሊሞች ላይ በከፈተው ድንገተኛ ተኩስ 51 ሰዎችን መግደሉን […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህግ ለማያከብሩ ከተሞች ከፌደራል የሚመደብላቸውን ፈንድ እንደሚያቋርጡ አሰጠነቀቁ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህግ ለማያከብሩ ከተሞች ከፌደራል የሚመደብላቸውን ፈንድ እንደሚያቋርጡ አሰጠነቀቁ:: ፕሬዚዳንቱ ሲያትል ፣ ፖርትላንድ ፣ ኒው ዮርክ እና ዋሽንግተን ከተሞችን በስም ጠቅሰው ህግ የማያከብሩ ከሆነ ከፌደራል የሚደረግላቸው የገንዘብ ድጋፍን እንደሚቆም የሚያስገነዝብ የውስጥ ማስታወሻ መፈረማቸው ተሰምቷል፡፡ በኔ አስተዳደር ከግብር ከፋዮች የሚሰበሰብ ዶላር ህገ ወጥ ትን ለማጠናከር አይባክንም ያሉት ትራምፕ እነዚህን ከተሞች […]

ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡ ህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ90 ሺህ በላይ አዲስ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ ብራዚልን ቀድማና አሜሪካንን ተከትላ ሁለተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ አሁን ላይ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሁለተኛዋ ሀገር ስትሆን፤ በሟቾች […]

ትራምፕ ኮሮረናቫይረስ አሜሪካዉያንን እንደጎዳ አመኑ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2012 ትራምፕ ኮሮረናቫይረስ አሜሪካዉያንን እንደጎዳ አመኑ::ሲ ኤን ኤን እንደዘገበዉ ትራምፕ ኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ እነደተገኘ በመጀመሪያዎቹ ሳመንታት ቫይረሱ አደገኛ እንደሆነ ያዉቁ እንደነበር ተናግረዋል ብሏል፡፡ትራምፕ ከታዋቂዉ ጋዜጠኛ ቦብ ዉድዋር ጋር ባደረጉት የድምጽ ቅጂ ቃለ ምልልስ ፤ ኮሮና ቫይረስ በጣም አደገኛ በትንፋሽ የሚተላለፍ ፤በፍጥነት የሚዛመት ከዚህ በፊት ከነበሩ ጎንፋኖች በጣም ገዳይ መሆኑን ያዉቁ እንደነበር […]

የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛው የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር መመዝገቡ እንዳሳሰበው ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛው የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር መመዝገቡ እንዳሳሰበው ገለፀ:: ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ በ24 ሰዓታት ውስጥ በዓለም ከ307 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መያዛቸው ሪፖርት ደርሶኛል ብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ከሁሉም ሀገራት የበለጠ ከፍተኛውን ቁጥር ያስመዘገቡት ህንድ አሜሪካና ብራዚል ናቸው፡፡ እንደሪፖርቱ በሳምንቱ መጨረሻ ህንድ 94 ሺህ 372፣ አሜሪካ 45 ሺህ 523፣ […]