loading
የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጅብ ራዛቅ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ21፣ 2012 የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጅብ ራዛቅ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ:: እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2009 እስከ 2018 ማሌዢያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ናጅብ በሰባት ክሶች ነው ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ናጅብ የቀረቡባቸውን ክሶች በሙሉ አልፈፀምኩም በማለት ቢቃወሙም አቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ በማስረጃ በማረጋገጡ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 10 ሚሊዮን ዶላር የመንግስት […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ሂዝቦላ በእሳት እየተጫወተ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 22፣ 2012 እስራኤል ሰሞኑን በድንበር አካባቢ ከሂዝቦላ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጓንና የተቃጣባትን ጥቃት በብቃት መመለሷን ተናግራለች፡፡ኔታኒያሁ በሰጡት መግለጫ የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ሉዓላዊ ድንበራችንን ጥሶ ለመግባት ሙከራ ማድረጉ በእሳት ጨዋታ መሆኑን ሊያውቅ ይባዋል ብለዋል፡፡ለሚቃጣብን ማንኛውም ጥቃት የምንሰጠው የአፀፋ ምላሽ የከፋ መሆኑን አውቆ ቡድኑ አደብ መግዛት አለበት ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው […]

ሩሲያ የመጀመሪያውን የኮቪድ19 ክትባት ለዓለም አበረክታለሁ እያለች ነው

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 የሞስኮ ባለ ስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ የኮሮናቫይረስን ክትባት ለመላው ዓለም ለማተዋወቅ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ብቻ ነው የቀራቸው፡፡ጋማሊያ ኢንስቲትዩት አገኘሁት ያለውን ክትባት ቢበዛ እስከ ኦገስት 10 ባለው ጊዜ ወስጥ ይፋ አደርጋለሁ ብላለች ሩሲያ፡፡ይሁን እንጂ ሩሲያ ስለ ክትባቱ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ከመስጠት መቆጠቧ የውጤታማነቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል የሚሉ ወገኖች ስጋታቸውን ቀድመው እየገለፁ ነው፡፡ሲ ኤን […]

በደቡብ ኮሪያ ደራሽ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት 13 ሰዎችን ገደለ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ28፣ 2012 በደቡብ ኮሪያ ደራሽ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት 13 ሰዎችን ገደለ:: በዋና ከተማዋ ሴኡል አቅራቢያ በሚገኙ አካባዎች የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ከሟቾቹ በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ትተው እንዲፈናቀሉ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ አንድ የ60 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 13 ሚሆኑ ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀም አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ ጎርፉ ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት እና […]

በሊባኖስ የሟቾች ቁጥር ከ130 በላይ ሲደርስ የቆሰሉ ሰዎች ከ5 ሺህ በላይ መሆናቸው ተነግሯል::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012በሊባኖስ የሟቾች ቁጥር ከ130 በላይ ሲደርስ የቆሰሉ ሰዎች ከ5 ሺህ በላይ መሆናቸው ተነግሯል:: በወደብ ተከማችቶ በነበረ ኬሚካል ፍንዳታ ሳቢያ ከሞቱት እና ከቆሰሉት ሰዎች ባሻገር 300 ሺህ ሊባኖሳዊያን ቤት አልባ መሆናቸውን የሀገሪቱ ቴሌቭዥን ዘግቧል፡፡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም በህንፃዎች ፍርስረሾች ስር ተቀብረው የቀሩ ሰዎችን ለማግኘት ፍለጋቸውን አጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው በተከሰተው ፍንዳታ ምክንያት […]

የህንድ የጎርፍ አደጋ ስጋት ህንድ ውስጥ የመሬት መንሸራተት ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደረሰ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 የህንድ የጎርፍ አደጋ ስጋት ህንድ ውስጥ የመሬት መንሸራተት ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደረሰ:: በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በአንድ የሻይ ማሳ ላይ በደረሰው በዚህ አደጋ እስካሁን የሟቾቹ ቁጥር 43 ደርሷል ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የመሬት መንሸራተት አደጋው መንስኤ በሀገሪቱ እየዘነበ ያለው ከባድ ዝናብ ሲሆን በአደጋው ሳቢያ ከ24 ሰዎች በላይ የገቡበት አልታወቀም፡፡ የሀገሪቱ […]

ፈረንሳይ በምስራቃዊ ሜዲትራንያን አካባቢ ወታደራዊ ሀይሏን ለማጠናከር እያሰበች ነው ተባለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 ፈረንሳይ በምስራቃዊ ሜዲትራንያን አካባቢ ወታደራዊ ሀይሏን ለማጠናከር እያሰበች ነው ተባለ:: ፓሪስ ሁለት ተዋጊ ጀቶችን ጨምሮ የባህር ሃይል እዝ ወደ ቀጠናው ለመላክ መዘጋጀን ተናግራለች፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፈረንሳይ ይህን የምታደርገው ቱርክ ወደስፍራው የጦር መርከቦችን መላኳን ተከትሎ በአንካራ እና በአቴንስ መካከል ውጥረት በመፈጠሩ ነው ተብሏል፡፡ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአካባው የተፈጠረው ሁኔታ በሁለቱ ሀገራት መካከል […]

ጀርመን ለሊባኖስ የምታደርገው ድጋፍ ገሀሪቱ ከምታርገው ሪፎርም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገለፀች::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 ጀርመን ለሊባኖስ የምታደርገው ድጋፍ ገሀሪቱ ከምታርገው ሪፎርም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገለፀች:: የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሄይኮ ማስ ድጋፉን አስመልክተው ሲናገሩ ቤይሩት ከደረሰባት አደጋ እንድታገግም ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለሚጠብቃት የፖሊሲ መሻሻያ ጭምር ነው የምንደግፋት ብለዋል፡፡ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ጀርመን በአደጋው ከባድ ጉዳት ለደረሰባት ቤይሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ1.18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በሊባኖስ ቀይ […]

ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይስን ለወራት ተቆጣጥራ ከቆየች በኋላ አዲስ ታማሚዎችን ማግኘቷ ትልቅ ስጋት ፈጥሮባታል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይስን ለወራት ተቆጣጥራ ከቆየች በኋላ አዲስ ታማሚዎችን ማግኘቷ ትልቅ ስጋት ፈጥሮባታል:: ሀገሪቱ ከ100 ቀናት በላይ ዜጎቿ ከኮቪድ19 ነጻ ሆነው የከረሙ ሲሆን ሰሞኑን አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ከሶስት ቀናት ባልበለጠ ገዜ የታማሚዎቹ ቁጥር ወደ 17 ከፍ ማለቱ መሰማቱን ሲ ጂ ቲ ኤን  በዘገባው አስነብቧል፡፡ የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደርን የበሽታው […]

የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ:: ቀዳማዊት እመቤቷ ፕሬዚዳንቱ ውጤት ያለው ስራ ሰርቶ ለማሳየት ከበቂ በላይ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ግን አንድም ፍርያማ ተግባር አላከናወኑም ብለዋል፡፡ ትራምፕ ለሀገራችን ትክክለኛው መሪ አይደሉም ያሉት ሚሼል አንድ ቀላል ምሳሌ ብናነሳ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በአሜሪካ የተከሰተውን ሁኔታ ማረጋጋት አልቻሉም […]