ትራምፕ ስደተኞችን ችሎታ እና እድሜ ላይ ባተኮሩ መስፈርቶች እንቀበላን አሉ፡፡
ትራምፕ ስደተኞችን ችሎታ እና እድሜ ላይ ባተኮሩ መስፈርቶች እንቀበላን አሉ፡፡ በስደተኞች ጉዳይ በብጥቅየሚተቹት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ስደተኞችን የምትቀበልበት አዲስ ፖሊሲ ለማውጣት አቅደዋል፡፡ በዚህም መሰረት ወደ አሜሪካ ለመግባት አንዱ መለኪያ ወጣትነት እንደሆነ ከዋይት ሀውስ የወጣው መረጃ ያሳያል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ወጣት መሆን በራሱ ግን ብቸኛ መስፈርት አይደለም፡፡ በተጨማሪም በትምህርታቸው የገፉ እና እንግሊዘኛን አቀላጥፈው የሚናገሩ ሰራተኞች […]
ኢትዮጵያ ተ.መ.ድ ኮቪድ-19ን ለመግታት የጀመረውን ኢኒሺየቲቭ እንደምትደግፍ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 ኢትዮጵያ ተ.መ.ድ ኮቪድ-19ን ለመግታት የጀመረውን ኢኒሺየቲቭ እንደምትደግፍ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ:: የተባበሩት መንግስታት ባለአደራ ፈንድ ለኮቪድ 19 ምላሽ ለመስጠት የጀመረውን “Rise for All” ኢኒሺየቲቭ ኢትዮጵያ መቀላቀሏን ፕሬዚዳንቷ ትናንት አስታውቀዋል።በተመድ ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና መሃመድ ይፋ የሆነው ፕሮጀክት የዓለም ሴት መሪዎች ወረርሽኙ ያስከተለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ለመግታት የሚረዳ መፍትሄ ለማበጀት ህብረታቸውን፣ ጥረታቸውንና ሃብታቸውን በማቀናጀትና በማንቀሳቀስ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል።ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በተጨማሪ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢርና ሶልበርግና የባርባዶስ አቻቸው ሚያ ሞትሊ የተ.መ.ድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሮች ፕሮጀክቱን ለመደገፍ የሚያግዝ የቪዲዮ ውይይት አድርገዋል። “ኮቪድ19 ዓለም አቀፍ ቀውስ መሆኑን ተከትሎ ምላሽ ለመስጠት መዘግየት ሞትን መጥት ነው፤ ሁላችንም ተመሳሳይ ጠላትን የተጋፈጥን በመሆናችን ሰብዓዊ አቅማችንን አንድ ላይ በማስተባበር ለውጤት መሰለፍ አለብን” ብለዋል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ። “ቫይረሱን በተናጠል ወይም በአንድ አገር ጥረት ብቻ መግታት ስለማይቻል ተመድ ጋራ ትብብር ያቀረበውን ጥሪ እደግፋለሁ” ብለዋል። የፈንዱ ግብ በመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት 1 ቢሊዮን ዶላር ማሰባሰብ ሲሆን በሁለት አመታት ውስጥ ደግሞ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ያለመ ነው።በዚህም ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን አገሮች፣ ህፃናትን፣ ሴቶችንና ለአደጋ የተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ አቅጣጫ ተይዟል።
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዓም መሪዎች መናበብ ባለመቻላቸው ህዝባቸውን ከኮቪ 19 መታደግ አቅቷቸዋል አሉ::
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 የተባበሩት መንግስታ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከቢቢ ጋር ባደረጉት ቀለ መጠይቅ መላው ዓለም በአንድነት ቢተባበር በሽታውን መግታት ይቻል ነበር ብለዋል፡፡የሀገራት መሪዎች እርስበርስ ተግባብተው እና አንድ ሆነው ከመስራት ይልቅ አንዱ በሌላው ላይ ጣት በመጠቋቆም በየራሳቸው መንገድ መጓዛቸው ጎድቷቸዋል ነው ያሉት ዋና ፀሀፊው፡፡ሁኔታው በጣም እንዳሳሰባቸው የገለፁት ጉቴሬዝ አሁንም ቢሆን አልረፈደም ተባብሮ […]
ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች::
ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች:: አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፉን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስረክቧል።ድጋፉ በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽን ለመከላከል ተግባራዊ ካደረጋቸው የድጋፍ ማዕቀፎች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም ነዉ ድጋፉን ያስረከቡት ፡፡ቫይረሱ በዓለም ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ያስታወሱት አምባሳደሯ፤አገራቸው ኢትዮጵያን ለመርዳት ድጋፉን ማድረጓን ገልጸዋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመዋጋት ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ፕሮፌሰርሂሩት፤ሳሙና የእጅ መታጠቢያ 213 ሺህ ኢንፍራሬድ ቴርሞሜትር 50 ያሕል ሰራተኞችችን ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የሚያስች ዋይፋ አፓራተስ አበርክተውልናል። እነዚህ ቁሳቁስ ለቴክኒክና ሙያ ተቋሞችና ለዩኒቨርሲቲዎች የምናሰራጫቸው ይሆናል።ብለዋልድጋፉ በትምህርት ተቋማት ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡
አቶ ገዱ የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን ዴቪድ ቢስሊይን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ ወገኖች የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት፣ የበረሃ አንበጣ እና የጎርፍ አደጋ በቀጠናው ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።በተጨማሪም የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታን በተመለከተ መረጃ […]
በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከአሜሪካ አልፎ ዓለም አቀፍ ይዘት እየተላበሰ ነው ተባለ::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከአሜሪካ አልፎ ዓለም አቀፍ ይዘት እየተላበሰ ነው ተባለ:: አሁን ላይ የጥቁሮች ህይዎት ያሳስበናል የሚለው ተቃውሞ ከአሜሪካ ከተሞች አልፎ በእግሊዝ፣ በጀርመን በኒው ውዚ ላንድ እና በሌሎች ሀገራትም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በቅርቡ በፖሊስ መኮንን የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ጉዳይ በኮሮናቫይረስ ለምትታመሰው አሜሪካ ሌላ ራስ […]
የአልቃይዳ የሰሜን አፍሪካ መሪ አብደልማሌክ ድሩክደል በፈረንሳይ ጦር ተገደሉ፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 የአልቃይዳ የሰሜን አፍሪካ መሪ አብደልማሌክ ድሩክደል በፈረንሳይ ጦር ተገደሉ፡፡ የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አብደልማሌክ ድሩክደል በሰሜናዊ ማሊ ግዛት በፈረንሳይ ወታደሮች መገደሉን አስታውቋል፡፡ እንደ አልጄዚራ ዘገባ የሰሜን አፍሪካ የአለቃይዳ አዛዥ በማሊ ለሰባት ዓመታት በፈረንሳይ ወታደሮች ሲታደን መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በሽብረተኛ ቡድን መሪው መገደል ዙሪያ ከአልቃይዳ በኩል ምንም የተባለ ነገር […]