loading
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተስተካካይ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

በ21ኛው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀግብር ቅዳሜ እና ዕሁድ ሀዋሳ ከተማ ላይ መካሄድ የነበረባቸው፤ ነገር ግን በደጋፊዎች ግጭት ምክንያት ያልተካሄዱ ሁለት ግጥሚያዎች ዛሬ ይከናወናሉ፡፡ ቅዳሜ መደረግ የነበረበት እና ከጨዋታው ጅማሮ በፊት በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ለዛሬ የተገፋው የደቡብ ፖሊስ እና ወላይታ ድቻ ፍልሚያ ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ ስታዲየም ይከናወናል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች […]

ባየርን ሙኒክ እና ላይፕዚህ በጀርመን ዋንጫ ፍፃሜ ተገናኝዋል

የዲ. ኤፍ. ቢ ዋንጫ ወይንም የጀርመን ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ማክሰኞ እና ዕረቡ ዕለት ተካሂደዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ በቮልክስፓርክ ስታዲየም አር. ቢ ላይፕዚህ ሀምቡርግን 3 ለ 1 ረትቶ ለፍፃሜ ዋንጫ ማለፍ ችሏል፡፡ ዩሱፍ ፖልሰን፣ ኢሚል ፎርስበርግ እና ቫሲሊጄ ያኒቺ በራሱ መረብ ላይ ላፕዚህን ለፍፃሜ ያበቁ ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ ትናንት ምሽት ደግሞ ዌሰር ስታዲየም ላይ ባየርን ሙኒክ ወርደር […]

ላትሲዮ ለኮፓ ኢታሊያ ፍፃሜ አልፏል፤ ዛሬ ተጋጣሚው ይለያል

የ2018/19 የጣሊያን ኮፓ ኢታሊያ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ትናንት ምሽት ሲደረግ፤ ዛሬ ሌላኛው ግጥሚያ የሚከናወን ይሆናል፡፡ በአሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ የሚመራው ኤስ ሚላን ጁሴፔ ሚያዛ ላይ የሮማውን ቡድን ላትሲዮ አስተናዶ የ1 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞት ለፍፃሜ ዋንጫው ሳይበቃ ቀርቷል፡፡ ላትሲዮም በደርሶ መልስ ጨዋታ የ1 ለ 0   ውጤት በማስመዝገብ የኮፓ ኢታሊያ ፍፃሜ ተፋላሚነቱን አረጋግጧል፡፡ የሮማውን ቡድን ወደ […]

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 36ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬን ጀምሮ ይካሄዳል

የዘንድሮው የሊጉ መርሀግብር ሊጠናቀቅ የሶስት ጨዋታዎች ዕድሜ የቀሩ ሲሆን የሊጉ አሸናፊ እና የቀጣይ ዓመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፊ ለመሆን የሚደረገው ፉክክር አጓጊነት በርትቷል፡፡ ዛሬ በሳምንቱ መርሀግብር ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ከሊጉ የተሰናበተውን ሀደርስፊልድ ታውን ምሽት 4፡00 ሰዓት ሲል ያስተናግዳል፡፡ ቀያዮቹ የተቀናቃኛቸውን ማንችስተር ሲቲ ነጥብ መጣል እየናፈቁ፤ የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ በሌሎቹ አሸናፊነታቸውን አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል፡፡ ነገ የሳምንቱ […]

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቐለ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

የሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በክልል እና አዲስ አበባ ስታዲየሞች ይከናወናሉ፡፡ ከአንድ ጨዋታ በስተቀር ሌሎች ግጥሚያዎች ክልል ላይ ይደረጋሉ፡፡ ክልል ላይ የሚከወኑት እነዚህ ጨዋታዎች በተመሳሳይ 9፡00 ይደረጋሉ፡፡ አዳማ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ በአሰልጣኝ ገዛህኝ ከተማ የሚሰለጥነውን ኢትዮጵያ ቡና የሚገጥም ይሆናል፡፡ ባህር ዳር ከነማ በግዙፉ የከተማው ስታዲየም ከሊጉ ላለመውረድ እየተፍጨረጨረ የሚገኘውን ደቡብ ፖሊስ ያስተናግዳል፡፡ […]