loading
ግብጽ ጥንታዊ ቅርሶቿን አስመለሰች፡፡

ግብጽ ከ500 ዓመት በላይ እድሜ ያላቸውን ቅርሶቿን ከእንግሊዝ መረከቧን የሀገሪቱ የባህል ሚኒስትር ኢሳም አብደል ዳይም ተናግረዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ቅርሶቹ የጥንታዊት ግብጽን ታሪኮች የሚያሳዩ የድንጋይ ላይ ጽሁፎችና ስዕሎች ናቸው፡፡
አብደል ዳይም እነዳሉት እነዚህ ጽሁፎች እና ስዕሎች በስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሙህዲን አል ካፊጂ በተባለ ጥበበኛ የተዘጋጁ ናቸው፡፡
ግብጽ ከ50 ዓመት በፊት ከ33 ሺህ በላይ የጥበብ ስራዎቿ እንደጠፉባት ይነገራል፡፡ እንግሊዝ ዉስጥ በርካታ የአፍሪካውያን ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ኢትዮጵያም ብዛት ያላቸው ቅርሶቿን ከእንግሊዝ ለማስለለስ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *