የፈረንሳይ መንግስት በነዳጅ ላይ ሊጥል ያሰበውን ታሪፍ ለጊዜው አዘግይቶታል
የፈረንሳይ መንግስት በነዳጅ ላይ ሊጥል ያሰበውን ታሪፍ ለጊዜው አዘግይቶታል
አርትስ 25/03/2011
ፓሪስ ቢጫ ሰደርያ በለበሱ የተቃውሞ ሰልፈኞች መጨናነቅ ከጀመረች ሁለት ሳምንታትን አስቆጥራለች፡፡
ምክንያታቸው ደግሞ የፈረንሳይ መንግስት በነዳጅ ምርቶች ላይ ቀረጥ ሊጥል ነው የሚል ዜና መሰማቱ ነው፡፡
ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው ሰልፈኞቹ በየጎዳናው ያገኙትን ቁሳቁስ ሁሉ ሲያቃጥሉ እና ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ሲገቡ ተስተውለዋል፡፡
ፖሊስም በተለያዩ የፈረንሳይ ከተሞች የንብረት ውድመት የሚያደርሱ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስና በውሀ በመበተን ስራ ላይ ተጠምዷል፡፡
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከተመረጡ ጀምሮ እንደዚህ የከፋ ተቃውሞ ገጥሟቸው አያውቅም እየተባለ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ በቤተ መንግስታቸው ባለ ስልጣኖቻቸውን ሰብስበው በጉዳዩ ዙሪያ በስፋት መክረውበታል፡፡
ማክሮን ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር ከተመካከሩ በኋላ በሚቀጥለው ወር በነዳጅ ምርቶች ላይ ሊጥሉት የነበረውን ቀረጥ ለማዘግየት ተገደዋል፡፡
ፖሊስ እስካሁን በአመፁ ከተሳተፉት መካከል ቀንደኛ የተባሉትን 378 ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዚህ ሳምንት ወደ ሰርቢያ ለሁለት ቀናት ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት በቀውሱ ሳቢያ መሰረዛቸውም ተሰምቷል፡፡