የየመን ተዋጊ ሀይሎች አዲስ ውይይት ጀመሩ፡፡
የየመን ተዋጊ ሀይሎች አዲስ ውይይት ጀመሩ፡፡
የየመን መንግስት እና የሁቲ ሚሊሻዎች ተወካዮች በዮርዳኖስ ኦማን ተገናኝተው በእስረኞች ልውውጥ ዙሪያ መምከር ጀምረዋል፡፡
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ውይይቱ ከእስር ተለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚቀላቀሉ እስረኞን ከመለዋወጥ ባሻገር ለቀጣይ ፖለቲካዊ ንግግር ያለው ፋይዳ ትልቅ ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ርድጅት የየመን ልዩ ልኡክ ማርቲን ግሪፊትዝ እና የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ፒተር ማውረር በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡
ልዩ ልኡኩ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ስብሰባ በርካታ መልካም ነገሮችን ለማምጣት እንነጋገራለን፤ ቀጣዩ ደረጃ እስረኞቹን ማስፈታት ይሆናል ብለዋል፡፡ከታሰሩት መካከል የሳወዲ አረቢያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሚገኙ ሲሆን እጣ ፋንታቸው የሚወሰነው በሳውዲ መራሹ ጦር የሚታገዘው የየመን መንግስት ባሰራቸው የሁቲ እስረኞች መለቀቅ ላይ ነው ተብሏል፡፡
የሁቲ ሚሊሻዎች ልኡካን ተወካይ የሆኑት አብደልከድር ሞርታዳ ከሩሲያ ቱደይ ጋር ባደረጉተረ ቃለ ምልልስ በየመን ለቀውሱ መባባስ ሳውዲ አረቢያ ዋና ተጠያቂ ናት ብለዋል፡፡
ተዋጊ ሀይሎቹ በሁዴይዳ ወደብ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ስምመነቱን ጥሰው ወደ ጦርነት የገቡ ሲሆን አንዱ ሌላውን ተጠያቂ ለማድረግም እርስበርሳቸው እየተካሰሱ ይገኛሉ፡፡
መንገሻ ዓለሙ