loading
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ለማ መገርሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ወደ አስመራ የተጓዙበት ጉዳይ በስኬት ተጠናቋል ተባለ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የሚመራውና የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን፣ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ- መንበር ኣቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራውና አቶ ኢብሳ ነገዎ፣ ኣቶ አቶምሳ ኩምሳ፣ ኣቶ ቶሌራ አደባ እና ኣቶ ገመቹ ኣያና የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ዛሬ በአስመራ ኤርትራ በመገናኘት ወንድማዊ መንፈስ በተንጸባረቀበትና በሙሉ መተማመን በተካሄደ የእርቅ ውይይት ያሉ ስምምነቶችና መግባባቶች ላይ ተደርሷል።
ሁለቱም ቡድን ስለኦሮሞና ኦሮሚያ እንዲሁም ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በውይይት ኣብረው ለመስራት ተስማምተዋል።
ለረዥም ዓመታት በኦነግና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የነበረው ጦርነት ተገትቶ ፡ ካሁን በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ሁኔታ ኦነግ በሃገር ውስጥ በግልጽ ሊሰራ የሚያስችለው መሆኑ ከግንዛቤ ገብቶ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ እንዲቀጥል ከስምምነት ተደርሷል።
በመጨረሻም ከስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ስራ ላይ እያዋሉ ምርመራና ጊዜ የሚጠይቁትን ቀስ በቀስ ለመጨረስ በቀጣይነት ከፍጻሜ የሚያደርስ ኮሚቴ በኣስቸኳይ እንዲቋቋም ተስማምተዋል።

ምንጭ ፦ የኦሮሞ ነፃነት ድምፅ ገፅ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *