loading
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ ትራንዚት ለሚያደርጉ መንገደኞች በከተማዋ የሚገኙ መስዕቦችን በነፃ ማስጎብኘት ጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ ትራንዚት ለሚያደርጉ መንገደኞች በከተማዋ የሚገኙ መስዕቦችን በነፃ ማስጎብኘት ጀመረ፡፡

አየር መንገዱ በመዲናዋ  ትራንዚት ለሚያደርጉ ዓለም አቀፍ መንገደኞቹ  የአዲስ አበባን የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች  በነፃ የማስጎብኘት ፕሮግራም የጀመረው  በዛሬው ዕለት ነው፡፡

አየር መንገዱ ለአርትስ በላከው መግለጫ ባለፍት የፈረንጆቹ  2017እና 2018 በአጠቃላይ 11 ሚሊየን መንገደኞችን ያስተናገደ ሲሆን ከ9 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ከውጭ ሀገር የሚመጡ እና ከአዲስ አበባ ወደሌሎች ሀገራት የሚጓዙ ናቸው፡፡

እነዚህ መንገደኞች እንደሚሄዱበት ሀገር ቅርበት እና ርቀት ይለያይ እንጂ ቀጣዩ በረራ እስኪደርስላቸው  በአየር መንገዱ  ውስጥ ለ6 እና 8 ሰዓታት ያህል መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡

ስለሆነም አየር መንገዱ አዲስ አበባን በመተላለፊያነት የሚጠቀሙ ደንበኞቹን ኤርፖርት ውስጥ የሚያሳልፉትን ሰዓት ተጠቅመው በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን መጎብኘት የሚያስችል ፕሮግራም ነው ከዛሬ ጀምሮ ይፋ ያደረገው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በመግለጫው እንዳሰፈሩት አየር መንገዱ ለሀገር ገፅታ ግንባታ እና በቱሪዝም ዘርፉ ጎብኚዎችን ለመሳብ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው ይህን የጉብኝት ፕሮገራም ያዘጋጀው ብለዋል፡፡

አየር መንገዱ  ባሳለፍነው ሳምንትም ለጎብኚዎች እና ለቱሪዝም ዘርፉ ይረዳል ያለውን ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ማስመረቁ ይታወሳል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *