የአውሮፓ የቱሪዝም እና የንግድ ተቋም የአፍሪካ ህብረት እና የአለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባ ከተማን “የአለም የባህል እና የቱሪዝም ከተማ” በማለት መምረጡን አሳውቋል፡፡
ለኢፌድሪ ፕረዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ለከንቲባ ታከለ ኡማ የአዉሮፓ ቱሪዝም አካዳሚ ሜምበር ሺፕ ሽልማት ሊሠጥ ነው፡፡
የአውሮፓ የቱሪዝም እና የንግድ ተቋም የአፍሪካ ህብረት እና የአለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን አዲስ አበባ ከተማን “የአለም የባህል እና የቱሪዝም ከተማ” በማለት መምረጡን አሳውቋል፡፡
ተቋሙ አዲስ አበባ በአህጉር ደረጃ ባሳየችው አንፃራዊ ሰላም ፣ የተረጋጋ የንግድና ቱሪዝም እንቅስቃሴ በተጨማሪም በከተማዋ የአለም አቀፍ ተቋማት በየወቅቱ መበራከት ምክንያት ይህን ሽልማት ለመስጠት መወሰኑንም አሳውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ላለው የተረጋጋ የንግድና ቱሪዝም ስርዓት መገንባት ላበረከቱት አስተዋፅዖም በEuropean Council on Tourism and Trade የሚሰጠውን “European Tourism Academic Member” የሚል ትልቅ የአባልነት እና የክብር ሽልማት ለኢፌዲሪ ፕረዝዳንት ለወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ታከለ ኡማ ለማበርከት በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣም ይጠበቃል፡፡