የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ እና የክልሎች ኅብረት ሥራ አበረታች ስራዎች ማከናወናቸው ተገለፀ
የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ እና የክልሎች ኅብረት ሥራ አበረታች ስራዎች ማከናወናቸው ተገለፀ
የፌደራል ኅብረት ሥራ ሴክተር የ2011 በጀት ዓመት የ8 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በተደረገበት ወቅት እንደተገለፀው የኅብረት ሥራ ኤጀንሲዎች እና የክልሎች ኅብረት ሥራ ማህበራት አበረታች ስራዎች ማከናወናቸው ተነግሯል፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዑስማን ሱሩር በ8 ወራት የሴክተሩ አፈጻጸም ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው መሆናቸውን በመገልፅ፤ ከኅብረት ሥራ ማጠናከር አንጸር ካፒታል በማሳድግ፣ ትርፍ ክፍፍል ከማሻሻል፣ የሀገር ውስጥ ግብይት መነቃቃት ፣ የግብርና ሜካናዜሽን መስፋፋ እና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ቁጥር ማደግ፣ እንዲሁም በቁጠባና ኢንቨስትመንት አንጻር ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት መሻሻል ከሚሹ ጉዳዮች መካካል የኅብረት ሥራ ብቃት ማረጋጋጥ እና ኦዲቲንግ አገልግሎት ረገድ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው በመድረኩ የተነሱ ጉዳዮች ሲሆን በአጠቃላይ ግን የሴክተሩ አፈጻጸም ከክልል ክልል መለያየት እንዳሳየ በውይይቱ ወቅት ተነሰቷል፡፡
በውይይቱ መጨረሻም በቀሪ ወራት ልዩ ትኩረት የሚሹ ተብለው የተለዩት ጉዳዮች የተገለፁ ሲሆን፤ኅብረት ሥራን ከማጠናከር አንጻር ስልጠናዎች መሰጠት እንደሚገባ እና የኅብረት ስራ ማህበራትን በባለሙያ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት በመስጠት የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡