የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው
የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ የምስራቅ አፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው
አርትስ 20/02/2011
እንደ ዥንዋ ዘገባ የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚያካሄዳቸውን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ለማሳደግ እንዲረዳው ቅርንጫፍ ቢሮውን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው፡፡
በአዲስ አበባ የሚከፈተው ቢሮ ኩባንያው በቀጣናው የሚያካሂዳቸውን ትላልቅ የባቡር፣ የአውሮፕላን ማረፊያ እና የመንገድ ፕሮጀክቶች በቅልጥፍና ለማከናወን ያስችለዋል።
ቢሮው የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል እንዲሁም የተሟሉ ዘመናዊ ላቦራቶሪዎች ይኖሩታል ተብሏል።
የኩባንያው የምስራቅ አፍርካ ስራ አስኪያጅ ዌይ ኪያንግዩ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተከትሎ በሀገሪቱ በርካታ ግንባታዎች እየተካሄዱይገኛሉ፤ ይህም ለኩባንያው ሰፊ የስራ እድሎች ፈጥሮለታል።
በቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ የተከናወኑና እየተከናወኑ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ውስጥ የ216 ኪሎ ሜትር የወልዲያ-መቀሌ የባቡር ፕሮጀክት፣ የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ፣ 78 ኪሎ ሜትርየአዲስ-አዳማ ፈጣን መንገድ እና የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ማስፋፊያ ግንባታ ይገኙበታል፡፡