የሴቶች ሹመት አሁንም ቀጥሏል
የሴቶች ሹመት አሁንም ቀጥሏል
አርትስ 16/02/2011
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት አዲስ ሴት ፕሬዝዳንት መርጧል፡፡
ትላንት በተካሄደው እና አንድ ሺ 50 አባላት ድምፅ በሰጡበት የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ምርጫ ሁለት ዕጩዎች የቀረቡ ሲሆን ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጥ 419 ድምፅ በማግኘት የንግድምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ወ/ሮ መሰንበት የቀድሞ የዓባይ ባንክ ፕሬዚዳንት የነበሩ ሲሆን አሁን የኒው ዳይሜንሽን የንግድ ሥራ አመራር አማካሪ ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡
ንግድ ምክር ቤቱን አቶ ኤልያስ ገነቲን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡