loading
የሰሜን ኮሪያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሩሲያ ገብተዋል

 

የሰሜን ኮሪያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ሩሲያ ገብተዋል

የሰሜን ኮሪያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢም ኮኸን  የሩሲያ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል፡፡

ኢም ኮኸን  ሩሲያና ሰሜንኮሪያ የኢኮኖሚና ባህል ትብብር  ስምምነት ፊርማ የተፈራረሙበትን 70ኛ ዓመት አስመልክቶ በተዘጋጀ ፕሮገራም ላይ የሚካፈሉ ሲሆን  በዋናነት ወደ ሩሲያ  ያቀኑት ግን በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ለመወያየት መሆኑን ሲጂቲኤን አስነብቧል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንትም ፕርዚዳንት ኪም ጆንግ ሩሲያን እንደሚጎበኙ ሞስኮ አረጋግጣ ነበር፡፡

ሩሲያ የሰሜን ኮሪያው መሪ በሞስኮ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደረጉ ማረጋገጫ የሰጠችው  ኪም ጆንግ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት  ዶናልድ ትራምፕጋር በቬትናም  ያደረጉት ውይይት ላይ አለመስማማታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ይህ ሁኔታም ሩሲያ አሜሪካን የሚጎዳ የዲፕሎማሲያዊ ፍላጎት አሳይታለች በሚል አሳምቷታል፡፡

የሩሲያ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃ መሰረትፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ የሩሲያ ጉብኝታቸውን የሚያካሂዱበት ፕሮግራም  ወደፊት ይፋ ይደረጋል ብሏል፡፡

የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ  ሚኒስትር ሪ ዮንግ ሆ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ  2018 ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በተመሳሳይ የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭም  በፒዮንግያንግ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ዘገባው የሲጂቲኤን ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *