የሞሮኮ አየር መንገድ ለዛሬ ተይዘው የነበሩ በረራዎችን ለመሰረዝ ተገዷል
ምክንያቱ ደግሞ አብራሪዎቹ የስራ ማቆም አድማ በመምታታቸው ነው ብሏል የሞሮኮ ሮያል አየር መንገድ በድረ ገጹ ባሰራጨው ጽሁፍ፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አብራሪዎቹ ስራ ለማቆም ያስገደዳቸው ላቀረቡት የደሞዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ ከአሰሪ ድርጅታቸው አጥጋቢ መልስ አለማግኘታቸው ነው፡፡
በድርጅቱና በሰራተኞቹ መካከል ለወራት የዘለቀ ድርድር ቢደረግም መግባባት አልተቻለም ብለዋል የአብራሪዎች ማህበር አመራሮች፡፡
አየር መንገዱም ሰራተኞቹ ወደ ስራ ገበታቸው በፍጥነት እንዲመለሱና የተስተጓጎለው የበረራ አገልግሎት እንዲጀመር ለማህበሩ ጥሪ ከማቅረብ በዘለለ ስለጥያቄያቸው የሠጠው ማብራሪያ የለም፡