loading
የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ውጤት ፍትሃዊ እንዲሆን  ሂደቱን እና የውጤቱን አሰባሰብ ዲጂታል ማድረጉን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡

የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ውጤት ፍትሃዊ እንዲሆን  ሂደቱን እና የውጤቱን አሰባሰብ ዲጂታል ማድረጉን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ ፕላን እና ልማት ኮሚሽን 4ኛ ዙር የህዝብ እና ቤት ቆጠራ በመጪው መጋቢት 29 ቀን 2011 ዓ.ም  ይካሄዳል ብሏል፡፡

ቆጠራው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በተመሳሳይ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

እያንዳንዱ ቤት እንዲቆጠር እና ቤት እንዳይዘለል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ቆጠራውን  ዲጂታል ለማድረግ 3.5 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

ከዚህ ቀደም ከነበሩ የህዝብ እና ቤት ቆተራዎች እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድ  ቆጠራውን ፍትሃዊ ለማድረግ ተሰርቷል ተብሏል፡፡

ለዚሁ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ከ180 ሺ በላይ ባለሞያዎች ማዘጋጀቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ሃላፊ ሚኒስትሯ ዶክተር ፍፁም አሰፋ እንደገለጹት የመጪውን ቆጠራ ውጤት ከዚህ ቀደም የነበሩት አይነት ቅሬታዎች እንዳያስነሳ ቆጠራውን የሚያማክሩ  የአማካሪ ምክርቤት ተቀዋቅሯል ብለዋል፡፡

በመደበኛ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ፣ በሆቴል፣ በሆስፒታል፣ በህፃናት ማሳደጊያዎች ፣በስደተኛ መጠለያዎች መጠለያ የሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች ፣በማረሚያቤቶች እና በገዳማት የሚኖሩ ሰዎች በቆጠራው የሚካተቱ ናቸው ተብሏል፡፡

በመሆኑም ለመጪው ቆጠራ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት የበኩሉን እንዲወጣ  የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ኤጀንሲ እና የብሄራዊ ፕላን እና ልማት ኮሚሽን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ዘገባዉ የሰላም ገብሩ ነዉ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *