loading
ዛሬ በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አንድ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በሀዋሳ ይካሄዳል

አርትስ ስፖርት 12/01/2011

በ2010 ዓ/ም ሳይጠናቀቅ ወደ 2011 ዓ/ም የተሸጋገረው የኢትዮጵያ ዋንጫ ወይንም የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ውድድር አንድ የሩብ ፍፃሜ እና ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይከናወናሉ፡፡
ሁሉም ጨዋታዎች በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እንዲካሄዱ የኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰነ ሲሆን፤ ከፌዴሬሽኑ በተገኘው መረጃ ጨዋታዎቹ በአዲስ አበባ ስታዲየም የማይካሄዱበት ምክንያት ሜዳው ለውድድሩ ብቁ ባለመሆኑ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መርሐ ግብር መሰረት ዛሬ ቀሪው የሩብ ፍፄው ጨዋታ በሲዳማ ቡና እና ቅ/ጊዮርጊዮርስ መካከል በ9:00 ሰዓት ይከናወናል።
በመጭው ማክሰኞም ውድድሩ ቀጥሎ በግማሽ ፍፃሜ 8:00 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከ ከመከላከያ፤ እንዲሁም የሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊ ከፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ጅማ አባጅፋር ጋር በ10:00 ሰአት በሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
የውድድሩ አሸናፊ በ2019 የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደር ሲሆን የጅማ አባ ጅፋር ክለብ በአፍሪካ ቻምፒንስ ሊግ ኢትዮጵያን ወክሎ ተካፋይ ይሆናል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *