ዛሬ በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተጎበኘዉ የቃሊቲ የፍሳሽ ማጣሪያ ሲጠናቀቅ 100 ሺህ ሜትሪክ ኪዩቢክ ውሃ ያክማል ተባለ፡፡
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የፍሳሽ ማጣሪያው ሲጠናቀቅም ለከተማ ግብርና አገልግሎት፣ አረንጓዴ ቦታዎችን ለመንከባከብ እና ለሌሎችም ተግባሮች ይውላል ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ አዲስ የተቋቋመው የውሃ እና ፍሳሽ ቦርድ አባላትም መገኘታቸውም ተነግሯል፡፡
ምክትል ከንቲባው ባለፈው ሳምንት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ የጎርፍ አደጋ የተከሰተበትን አካባቢ የጎበኙ ሲሆን በአደጋው የተፋናቀሉ ነዋሪዎችን ለማቋቋም አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።በጎርፍ አደጋው 526 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
አርትስ 24/12/2010