ዛሬ ምሽት ተጠባቂ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ይከናወናሉ
ዛሬ ምሽት ተጠባቂ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ይከናወናሉ
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ወደ ሩብ ፍፃሜ ለማለፍ የሚደረጉ የጥሎ ማለፍ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬም ይደረጋሉ፡፡
ፈረንሳይ ላይ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን በፓርክ ደ ፕሪንስ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ከሳምንታት በፊት ኦልድ ትራፎርድ ላይ ተገናኝተው፤ በፓሪሱ ቡድን የ2 ለ 0 ሽንፈት የገጠመው ማንችስተር ወደ ሩብ ፍፃሜው ለማለፍ 3 ለ 0 እና ከዚያ በላይ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ይጠበቅበታል፡፡
አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ውጤቱን መቀልበስ የማይቻል እንደሆነ ተናግሯል፡፡
በምሽቱ ዩናይትድ የፖል ፖግባ፣ አሌክሲስ ሳንቼዝ፣ አንቶኒ ማርሽያል፣ ፊል ጆንስ፣ ጄሴ ሊንጋርድ፣ ዩሃን ማታ፣ አንደር ሄሬራ፣ ኒማኒያ ማቲች እና ማቲዎ ዳርሚያን በቅጣት እና ጉዳት ምክንያት ግልጋሎት የማያገኝ ይሆናል፡፡
በባለሜዳው ፒ.ኤስ.ጂ በኩል ኔይማር አሁንም በጉዳት ምክንያት የማይሰለፍ ሲሆን ሌላኛው አጥቂ ኢዲንሰን ካቫኒ ጉዳይ አጠራጣሪ ሁኗል፡፡ ጨዋታው ምሽት 5፡00 ላይ ይከናወናል፡፡
ሌላኛው ግጥሚያ ደግሞ በተመሳሳይ ሰዓት ፖርቱጋል ምድር ላይ ፖርቶ በእስታዲዮ ዶ ድራጋኦ ሮማን ያስተናግዳል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ሮም ላይ ሲጫወቱ አሸናፊ የነበረው የጣሊያኑ ቡድን (2 ለ 1) ሲሆን ውጤቱ በፖርቶ የ1 ለ 0 ድል መቀልበስ የሚችል ነው፡፡
በምሽቱ ወደ ሩብ ፍፃሜው የትኛው ቡድን ይቀላቀል ይሆን…? የእርስዎን ግምት ይንገሩን?