እንግሊዝ ሁለት ሩሲዊያን ላይ ጣቷን ቀስራለች፡፡
አርትስ 30/12/2010
ለንደን ከሞስኮ ጋር የተካረረ ግጭት ውስጥ ያስገባትን የቀድሞው የሩሲያ ሰላይ ሰርጌይ ስክሮፓልን መርዘዋል ያለቻቸውን ሁለት ሩሲያዊያን ስማቸውንና ምስላቸውን ይፋ አድርጋለች፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው እንግሊዝ አሌክሳንደር ፔትሮቭ እና ሩስላን ቦሽሮቭ የተባሉትን ሩሲያዊያን ተጠርጣሪወች አሳልፋ እንድትሰጣት ለሩሲያ ጥያቄ ማቅረቧም ተሰምቷል፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ ግለሰቦች የተጠቀሙበት ስም ትክክለኛ አይደለም የሚል ጥርጣሬም አለ፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንግሊዝ የእንዚህን ግለሰቦች ስም እና ፎቶግራፍ ማሰራጨቷ ነገሩን ከሞስኮ ጋር አያገኘናኘውም ብሏል፡፡
ለንደን ግን እነዚህ ሰዎች ምናልባት በአውሮፓ ሲዘዋወሩ ከተገኙ በሚል ጥርጣሬ ለአውሮፓ ህብረት ሀገሮች የማደኛ እና የመያዣ ትዕዛዝ በትናለች ነው የተባለው፡፡