loading
‹‹አክቲቪስቶች የሀሳብ ገበሬዎች ናቸው፡፡ የሚዘሩት የሀሳብ ዘር የህብረተሰቡን ጥቅም የሚያስከብር መሆን አለበት::›› ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው

‹‹የአማራ ብሔረተኝነት ለጠንካራ አንድነት!›› በሚል መሪ ሀሳብ የዐማራ ማህበራዊ ሚዲያ አራማጆችና የፖለቲካ ተንታኞች የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ አቫንቲ ሆቴል እየተካሄደ ነው።
የምክክር መድረኩን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስጀምረውታል፡፡ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪ በአክቲቪስቶች እየተወከለ ስለሆነ ለህዝብ ጥቅም ስንል ኃላፊነታችንን እንወጣ፡፡ህዝቡ የሚፈልገውን ጥቅም ለማስከበር ምክንያታዊ አስተሳሰብ ያለው የሚዲያ አራማጅ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
አክቲቪስቶች የሀሳብ ገበሬዎች ናቸው፡፡በመሆኑም የሚዘሩት የሀሳብ ዘር የህብረተሰቡን ጥቅም የሚያስከብር መሆን አለበት ነው ያሉት፡፡እንቅስቃሴው ፍሬያማ እንዲሆን መንግስትና አክቲቪስቶች በተቀናጀ መንገድ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

አብመድ

አርትስ 25/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *