አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
በበርካታ ፊልሞች ላይ በትወና የሚታወቀው አርቲስት ተዘራ ለማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው አርቲስት ተዘራ ለማ ትናንት ምሽት ቤቱ ውስጥ እያለ በድንገት ህመም ካጋጠመው በኋላ በአካባቢው ወደሚገኝ የህክምና ማዕከል ቢወሰድም ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
“ውሳኔ ፊልም” ላይ መጀመሪያ የትወና ስራውን የሰራው አርቲስት ተዘራ ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ወክሎ ተጫውቷል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ፥ ፍቅር ባጋጣሚ ፣ ታስጨርሽኛለሽ፣ ፍቅር በይሉኝታ፣ አልወድሽም፣ ወንድሜ ያቆብ፣ ኢንጂነሩ እና ጥቁር እና ነጭ ተጠቃሽ ናቸው።
አርቲስት ተዘራ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።