loading
አምባሳደር ብርሃነ በአዲስ አምባሳደር ሊተኩ ነው፡፡

አርትስ 30/12/2010
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የሚያገለግሉትን አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስን አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እንዲተኳቸው ተወስኗል፡፡
ባለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ተልዕኮ ውስጥ ቆይታ የነበራቸው አቶ ብርሃነ ላለፉት ሁለት ዓመታት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት እያገለገሉ ከሚገኙበት ቻይና እንዲመለሱ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጠራታቸው ታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአምባሳደር ብርሃነ በተጨማሪ በብራዚል፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በካናዳና በሌሎች አገሮች የሚገኙ አምባሳደሮች ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሠረት ተተኪ አምባሳደሮች እየተመደቡ ሲሆን፣ አቶ ሱሌይማን በቻይና እንደሚመደቡ ተነግሯል፡፡ አቶ ሱሌይማን በናይጄሪያ፣ በጂቡቲና በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ሠርተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *