loading
አለም አቀፍ የፖስታ ህብረት ተቋማዊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ውይይት ጀምረ::

አለም አቀፍ የፖስታ ህብረት አባል ሀገራት በተቋሙ እኩል የመወሰን ስልጣንእንዲኖራቸው በሚያስችል የማሻሻያ ሀሳብ ላይ ነው ውይይቱ የጀመሩት፡፡
በውይይቱ ላይ 192 የህብረቱ አባል ሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
የህብረቱ ዳይሬክተር ጀነራል በሽር ሁሴን እንደተናገሩት አባል ሃገራቱ በህብረቱ ጉዳዮች ላይ እኩል የመወሰን ስልጣን ይኑራቸው የሚለው የውይይቱ አብይ አላማ ሲሆን ሌሎችም ተቋሙን የማሻሻያ ሃሰቦች ይነሱበታል ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በበኩላቸው የፖስታ አገልግሎት ማህበራዊ ሕይወት ትስስርን በማጠናከር ያለውን ሚና ገለፀው አገልግሎቱን ከሃገራዊ እቅዶች ጋር አስተሳስሮ ለምጣኔ ሀብት እድገት እንዲውል መደረግ አለበት ብለዋል፡፡
ኢትዮጲያ የፖስታ ህብረት አባል ከሆነች ዘንድሮ 110ኛ አመቷን ይዛለች ከኤዜአ እንደገለጸዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *