አሁን ካለው ሰንደቅ አላማ የተሻለ ሃሳብ ካለ ሰንደቅዓላማችን ይቀየራል ተባለ
አርትስ 14/01/2011 ዓ.ም
ይህንን ያሉት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሸታዬ ምናለ ናቸዉ፡፡ወ/ሮ ሽታዬ ዘንድሮ ለ11ኛ ግዜ የሚከበረዉን የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ፤ በዋናነትም በበዓሉ ከሰንደቅ ዓላማ ጋር የተያያዙ አመለካከቶችን ለመቅረፍ ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡
በውይይቱም የተለያዩ የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ምሁራን ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
አሁን ያለውን የሰንደቅዓላማ ሃሰብ የሚያስቀይር የተሻለ አሸናፊ ሀሳብ ከመጣ በአሸናፊው ሀሳብ መሰረት ባንዲራው የሚቀየር ይሆናል ሲሉ ምክትል አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ ልዩነቶች መኖራቸውን የተናገሩት ሃለፊዋ፤ አሁን ስራ ላይ ያለው ሰንደቃለማ የብሔር ብሔረሰቦችን አንድነት እና መቻቻል የሚያሳይ ነው ፤ ነገር ግን ከዚህ የተሻለ ሐሳብ ከመጣ መንግስት ለመቀበል ዝግጁ እንደሆነ ግልፀዋል፡፡
ይህ አስኪሆን ድረስ ግን አሁን ሥራ ላይ ያለው ሰንደቃላማ እንደነበረ ይቆያል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የዘንደሮ የሰንደቃላማ ቀን ˝ሰንደቅ አላማችን ለዲሞክራሲያዊ አንድነታችን ˝በሚል መሪ ቃል በመጪው ጥቅምት 5 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልል ከተሞች ይከበራል ተብሏል፡