በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በአዲሱ ክትባት ሁለት ሰዎች ከኢቦላ ቫይረስ ነጻ ሆነዋል::
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ክትባት ውጤት እያሳየ መምጣቱን የሃገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አታውቋል፡፡
በቫይረሱ ተይዘው የሙከራ ክትባቱን ሲወስዱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ከበሽታው ነጻ ሆነው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ መደረጉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው ሁለቱ ሰዎች በተሰጣቸው ህክምና መዳናቸውን ተከትሎ ዓለማችን በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አዲስ ተስፋ ሰንቃለች ብለዋል፡፡