loading
በዲላ ከተማ በኤሌክትሪክ አደጋ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት አለፈ

በዲላ ከተማ በኤሌክትሪክ አደጋ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት አለፈ

አርትስ 19/02/2011

የዲላ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ምክትል ሳጅን ጴጥሮስ ዘለቀ እንደገለጹት፥ አደጋው ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥቅምት 17 ቀን 2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 5 ሰዓት ገደማ የተከሰተ ሲሆን መንስኤውም ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር የተገናኘ የልብስ ማስጫ ላይ የተሰጣ ልብስ ለማስገባት ሲባል ነው፡፡

በዲላ ከተማ በተለምዶ ሞላ ጎልጃ ሰፈር ከሚባለው የከተማው ክፍል  በሚገኝ አንድ የቤተሰብ ቤት ወላጅ እናትን ጨምሮ የሁለት ሴት እና የአንድ ወንድ ልጅ በድምሩ አራትየአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቀዋል።

ሌላ አንድ የቤተሰብ አባል በኤሌክትሪክ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ጽኑ ህሙማን ክፍል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑንምአብራርተዋል።

ምክትል አዛዡ ህብረተሰብ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋር ተያይዘው ያሉ ነገሮች ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *