በኮዬ ፈጨ ሳይት 10 ሺሕ 955 የ20/80 ቤቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተነገረ
አርትስ 21/02/2011
በአዲስ አበባ የአቃቂ ቃሊቲ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በኮዬ ፈጨ ሳይት 10 ሺህ 955 የ20/80 ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል ፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈትቤት የኮዬ ፈጨ ሳይት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ንጉሤ ጸጋዬ እንዳስታወቁት ቤቶቹን ለመገንባት ገና ከጅምሩየመሰረተ ልማት፣ዲዛይን፣የግብዓት አቅርቦት፣የተሟላ የባለሙያ እጥረትና የዋጋ ግሽፈት ችግሮች ያጋጠመ ቢሆንም እነዚህን ተቋቁመን ግንባታዎቹንከ95 ከመቶ በላይ አድርሰነዋል ብለዋል፡፡
ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም ቤቶቹ ሁሉንም ዓይነት የመኖሪያ ቤት ያካተቱ ሲሆን በአጠቃላይ 10ሺሕ 955 የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ሱቆችተገንብተው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው ብለዋል፤በዚህ ዓመት የ20/80 ተመዝጋቢዎች የቤት ዕድለኞች እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡