loading
በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደረሰ::

በ24 ሰዓታት ውስጥ በ912 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ሁለት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 7 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል፡፡ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ በበሽታው ተይዘው እንክብካቤ ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል 66 ሰዎች ማገገማቸው ተሰምቷል፡፡በ24 ሰዓታት ምርመራ በቫይረሱ ተይዘው የተገኙት ሁለቱ ግለሰቦች ከነንያ እና ከፑንትላንድ የተመለሱ እና ሁለቱም በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው፡፡ሁለቱም ግለሰቦች ወንዶች እና የ20 እና የ25 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትየዮጵያዊያን መሆናቸውም ታውቋል፡፡ኢትዮጵያ እካሁን ለ18 ሺህ 754 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረጓን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *