በአገራችን ከተንዳሆ እና ከሰም ቀጥሎ ብዙ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው የርብ መስኖ ግድብ ተመረቀ
በአገራችን ከተንዳሆ እና ከሰም ቀጥሎ ብዙ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው የርብ መስኖ ግድብ ተመረቀ
አርትስ 18/02/2011
ከአስር ዓመት በፊት መሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የርብ መስኖ ግድብ በደቡብ ጎንደር ዞን እብናትና ፋርጣ ወረዳዎች መሀል ይገኛል። 75 ሜትር ከፍታ፣800 ሜትር ርዝመት ያለውና ከ235 ሚሊየን ኩዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ነው።
የፋርጣ፣ የእብናት፣ የፎገራ እና የሊቦ ከምከም ወረዳዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በምረቃው ላይ ተገልጿል::
የግድቡም ጠቀሜታዎች :- 20ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት ከ25 ሺህ በላይ አባወራ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፤ በክረምት ወራት ህዝቡን ሲያሰቃይ የነበረውን የጎርፍ ችግርን ይከላከላል፤ የተመጠነ ውሃ ዓመቱን በሙሉ ለጣና ሃይቅ ይመግባል፤ ለአካባቢው ማህበረሰብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ያስገኛል፤ በአሳ ልማት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ግድቡን ሲመርቁ አገራችን የውሃ ማማ ብትሰኝም ካለን የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሃ ጥቅም ላይ የዋለው ጥቂቱ ነው ብለዋል። በተለይም እንደ አዲስ የተቋቋመው የመስኖ ኮሚሽን በዚህ ረገድ ሚናውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በተለያዩ ክልሎች የመስኖ ግድብ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ሲሆን ይህም እየባከነ ያለውን ከ105 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት የሚችል ውሃ በመጠኑ ለመጠቀም ያስችላል ተብሏል።
ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ