በአንድ ቀን ልዩነት 2ኛው ናይጄሪያዊ ህገ-ወጥ ገንዘብ ይዞ ወደ ሌጎስ ሊሄድ ሲል ተያዘ፡
ተጠርጣሪ ኡቼ ኢማ የተባለ ናይጀሪያዊ የትራንዚት መንገደኛ፤ ህገ-ወጥ 8ሺህ 500 የአሜሪካ ዶላር ይዞ በአዲስ አበባ ኤርፖርት መያዙን በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አሳወቀ፡፡
የማለፊያ ቁጥሩ 06012483 እና ዲክሌር ቁጥሩ 003943 የሆነው ናይጀሪያዊ በአዲስ አበባ ኤርፖርት ትራንዚት ወይም መሸጋገሪያ አድርጎ ወደ ሌጎስ ሊሄድ ሲል በነበረው ብርቱ ቁጥጥር መያዙን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል፡፡
በተመሣሣይ፤ ተጠርጣሪ ኢፋኒቸኩ አማኑኤል ኢኬዲቡ የተባለ ናይጀሪያዊ መንገደኛ፤ ህገ-ወጥ 141ሺህ ዶላር ይዞ በቦሌ ኤርፖርት በኩል አድርጎ ወደ ናይጀሪያ ሊወጣ ሲል ታኅሣሥ 20/2011 ዓ.ም. በኤክስሬይ የፍተሻ ማሽን አማካኝነትና በጉምሩክ ሠራተኞች እንዲሁምበብሔራዊ መረጃ ደኅንነት ባለሙያዎች ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ ተይዟል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቁጥጥርን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ሲሆን ህብረተሰቡም ህገ-ወጦችን በመጠቆም እና በማጋለጥ እንዲተባበር ጥሪውን አቅርቧል፡፡