በአንበጣ መንጋ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሦ-አደሮች በዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ገልጹ፡፡
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 በአንበጣ መንጋ ጉዳት የደረሰባቸውን አርሦ-አደሮች በዘላቂነት ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ገልጹ፡፡
የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በቅርቡ በአካባቢዉ በተከሰተዉ የአንበጣ መንጋ ምክንያት በ35 የ1ኛ ደረጃ እና በአንድ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት-ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በኢኮኖሚና በሰነልቦና ተጎጂ መሆናቸውም ነው በጥናቱ የተመላከተው፡፡ 9ሽህ 388 ህፃናት እና 2 ሽህ 337 አጥቢና ነፍሰጡር እናቶችም የችግሩ ተጋላጭ መሆናቸውም ታውቋል፡፡
ታዲያ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ለተጎጂዎቹ ከሚደረግ የዕለት የምግብ ድጋፍ ባሻገር በአጭር ጊዜ በመስኖ እና በበልግ አልምተው ዘላቂና አስተማማኝ ንሯቸውን የሚመሩበትን ጥናትና እቅድ በማዘጋጀት በዞኑ ከሚገኙ ግበረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በደሴ ከተማ ምክክር አካሂዷል፡፡እንደ ግብርና መምሪያው ጥናት 3 ሽህ 847 ሄክታ መሬትን በዘመናዊ መስኖ በማልማት በአጭር ጊዜ ማምረት የሚቻልበት ስልት ተዘጋጅቷል፡፡
ለዚህም 107 ሞተር ፓምፕ፣29 ኩንታል የተሻሻለ የአትክልት ዘር እና 1ሽህ 450 የሰብል ምርጥ ዘር ከሚያስፈልጉት የመስኖ ቴክኖሎጂዎችና ግብአቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡እንደ ግብርና መምሪያ ጥናት፡ለዚህም ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግም ነው የተገለፀው፡፡
በውይይቱ የተሳተፉት የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ተወካዮች የጉዳቱ ሰለባ የሆኑትን አርሦ-አደሮች በአጭር ጊዜና በዘላቂነት ለማቋቋም የተያዘውን እቅድ እንደሚቀበሉትና በግብአት ፣በቴክኖሎጂና በሙያ ጭምር የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግም መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡