በቡራዩ በተነሳው ግጭት ተሳትፈዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ ከ300 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
አርትስ 07/01/2011 ዓ.ም
በቡራዩ በተነሳው ግጭት ከ300 እስከ 400 ሚሆኑ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ሲውሉ በአዲስ አበባም 300 ወንጀለኞች መያዛቸውን ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማል ተናገሩ፡፡
ኮሚሽነሩ ወንጀለኞች ከዜጎች ላይ የሰበሰቧቸውን ንብረቶች በየጫካ ውስጥ ደብቀው ተይዟል ፖሊስም እየሰበሰበ ነው ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ ከጥበቃ አባላት ጎን በመቆም ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረብ እንዳለባቸው እና ወጣቶችም ሰላምን ለማይፈልጉ አካላት መጠቀሚያ መሆን እንደሌለባቸው ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡በመግለጫቸው ላይ የመንግስት ትዕግስት ገደብ እንዳለው በመግለፅ ጉልበተኞችን እንደማይታገስ አስታውቀዋል።
በተያያዘም በአዲስ አበባ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰዉን ጥቃት በመቃወም ነዋሪዎች ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ነዋሪዎቹ ጥቃት ሲፈጸም ፖሊስ አልደረሰለንም ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡