loading
በህዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያሉ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 በህዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያሉ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡ የውይይቱ ዓላማ በግድቡ ዙሪያ በእውነታ ላይ የተመሰረተና ትክክለኛ መረጃን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስተላለፍ ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ በዌብናር የተካሄ ሲሆን በውይይተቱ ከተሳተፉት መካከል በሀገር ውስጥና በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም አሜሪካዊያን ይገኙበታል፡፡

ተወያዮቹ በዋናነት በግድቡ የሚሞላው ውሀ ሃይልን አመንጭቶ ከማለፍ የዘለለ ለሌላ ጥቅም የማይውል መሆኑና ይህም የታችኛውን ሀገራት እንደማይጎዳ አንስተዋል፡፡ ግድቡ በቀጠናው ያስከትላል የተባለው ተፅዕኖ እውነት አለመሆኑን ማስረዳት የሚችሉ የድንበር ተሸጋሪ ወንዞች ባለሞያዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

ውይይቱን ከተሳተፉት በአሜሪካን ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መካከል የፒ 2 ፒ መስራችና ፕሬዚዳንት ዶክተር እናውጋው መሃሪ አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂኔር ስለሺ በቀለ ጋተባዥ ነበሩ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከ60 እስከ 645 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን በመደበኛነት የኤሌክትሪክ አቅርቦት የማያገኙ ሲሆን የግድቡ ስራ ላይ መዋል ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡ በውይይቱ እንዲሳተፉ ግብዣ የቀረበላቸው የግብፅና ሱዳን ተወካዮች ለመሳተፍ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *