loading
ስፔን ከሶስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሰው ሳይሞትባት 24 ሰዓታት ተቆጥረዋል::

ስፔን ከሶስት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሰው ሳይሞትባት 24 ሰዓታት ተቆጥረዋል:: በስፔን የኮሮናቫይረስ እንደከተሰተ የመጀመሪያው ሞት በፈረንጆቹ ማርች 3 ቀን ነበር የተመዘገበው፡፡ቀስበቀስ የበሽታው ስርጭት እየተስፋፋ መጥቶ ስፔን በርካታ ዜጎቿን በቫይረሱ ምክንያት አጥታለች፡፡
አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በሀገሪቱ ታሪክ በ24 ሰዓታት ውስጥ በጣም ከፍተኛው የሞት መጠን 950 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡


የሀገሪቱ የአስቸኳይ የጤና ጉዳዮች ምላሽ ሀላፊ ፌርናንዶ ሲሞን አሁን ላይ ያየነው መሻሻል በጣም የሚያበረታታ ነው በማለት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡
ስፔን የጀመረችውን ቀስ በቀስ የእንቅስቃሴ እገዳዎችን የማላላት ዕቅዷን የገፋችበት ሲሆን ከቅርብ ቀናት ወዲህ የታማሚዎችም ሆነ የሟቾች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ይበልጥ አጋዥ ሁኔታዎችን ፈጥሮልኛል ብላለች፡፡እስካሁን በስፔን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከ286 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ ከነዚህ መካከል
ከ27 ሺህ በላይ የሚሆኑት መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *