loading
ሰርጌይ ላቭሮቭ ሶሪያን ለሶሪያዊያን እናስረክብ እያሉ ነው።

ሰርጌይ ላቭሮቭ ሶሪያን ለሶሪያዊያን እናስረክብ እያሉ ነው፡፡

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ሰሜናዊው የሶሪያን ክፍል ለበሽር አል አሳድ  መንግስት  ካላስተላለፍን በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም  ሊመጣ እንደማይችል ተረድተናል ብለዋል፡፡

ላቭሮቭ ይህን ያሉት አሜሪካ በሶሪያ ሰሜናዊ ድንበር አካባቢ በቱርክ መንግስት የሚተዳደር የፀጥታ ቀጠና ያስፈልጋል ማለቷን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ቱርክ እና አሜሪካ ተመካክረው በሰሜናዊ ሶሪያ ድንበር የአንካራ መንግስት የሚቆጣጠረው የፀጥታ ቀጠና ለማቋቋም ተስማምተዋል፡፡

ይሁን እንጂ በአሜሪካ መንግስት የሚደገፉት የኩርድ ታጣቂዎች ሀሳቡን ውድቅ አድርገውታል፡፡  ምክንያታቸው ደግሞ በቀላሉ ከቱርክ ጥቃት ይደርስብናል የሚል ነው፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ የረጂም ጊዜ ወዳጅ የሆነችው ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ ከአሜሪካ እና አጋሮቿ ጋር በሀሳብ ተስማምታ አታውቅም፡፡

አሁን በሶሪያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ታይቶበታል ያሉት ላቭሮቭ በሀገሪቱ ሽብርተኝነትን እስከመጨረሻው መዋጋት ግን ግድ ነው ብለዋል፡፡

ላቭሮቭ በተለይ ባለፈው ወር ሙሉ በሙሉ በጂሀዲስቶች እጅ የወደቀችው የኢድሊብ ግዛት ጉዳይ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *