loading
መንግስትና የጋምቤላና አፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ታረቁ

መንግስትና የጋምቤላና አፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ታረቁ

የኢትዮጵያ መንግስት ከጋምቤላና ከአፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ጋር የእርቅ ስምምነት መፈረሙ ተነገረ።

ስምምነቱ የተፈረመው በአስመራ ከተማ ከሁለቱ ፓርቲዎች ጋር በተደረገ ውይይት ነው ተብሏል።

ስምምነቱ የተፈረመው የአገር መከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድና የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ኡስማን መሀመድ ሁመዳ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ፣ በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የድርጅቶቹ ተወካዮች በተገኙበት መሆኑ ታውቋል።

ከጋምቤላና ከአፋር ነፃ አውጪ ንቅናቄዎች ጋር በተናጠል የተደረሰው ይኸው ስምምነት ንቅናቄዎቹ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ያደርጋቸዋል ተብሏል። ዜናው የኤፍቢሲ ነው።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *