ሐሰት: ፕሬዚዳንት ሣህል ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት ነው አላሉም።
ምስሉ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የ2014 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ነው።
በአማርኛ የተጻፈው ልጥፍ “#ሰበር #ዜና
ለመጀመሪያ ጊዜ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህል ወርቅ ዘውዴ እውነት ተናገሩ ይሄ ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት ነው በማለት ለፈረንሳይ መጽሔት ገልፃለች” ይላል።
እ.ኤ.አ ህዳር 22-2021 War in Ethiopia: the disarray of President Sahle-Work Zewde በሚል ርእስ JeuneAfrique የተሰኘው የፈረንሳይ መፅሄት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በመጥቀስ ጽሁፍ አውጥቷል።
እ.ኤ.አ ህዳር 24-2021 በፋና ድህረገፅ ላይ እንደወጣው መረጃ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚህ የፈረንሳይ መጽሔት ላይ የወጣውን ጽሁፍ ውድቅ አድርገዋል።
ፕሬዝዳንቷ ስለዚህ ፅሁፍ ሲናገሩ “ደራሲውን አግኝቼው አላውቅም። የፅሁፉን መልክ እንዲሁ በአጋጣሚ የተከሰተ እንደሆነ አድርጌ አልመለከተውም ። በኢትዮጵያ አመራር መካከል ልዩነት ለመፈጠር የሚደረግ ሙከራ እንደሆነ እገነዘባለሁ።” ብለዋል።
መንግስት ከህወሓት አማጽያን ጋር እየተካሄደ ያለው ጦርነት ሕግ የማስከበር ዘመቻ ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያ ገልጿል።
የጎግል የምስል ፍለጋ (google reverse image search) ውጤት እንደሚያሳየው በልጥፉ ላይ የተጠቀመው ምስል ከፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የፌስ ቡክ ገፅ የተወሰደ ሲሆን፣ ምስሉ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የ2014 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ሲከፍቱ ያደረጉትን ንግግር የሚያሳይ ነው።
ፕሬዚዳንቷ በንግግራቸው የመንግስትን የ2014 የስራ ዕቅድ አቅርበዋል። ለመጪዎቹ አምስት ዓመት የሚቆየዉ የሁለቱ ም/ቤቶች መከፈት በየዓመቱ ከሚደረጉት የመክፈቻ ሥነ- ሥርዓቶች በብዙ አንጻር ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው፡፡ ፕሬዚዳንቷ አጽንኦት እንደሰጡት የምክርቤቶቹ መከፈት የአንድ ምዕራፍ መጠናቀቅና የአዲስ ምዕራፍ መከፈትን የሚያበስር ነው፡፡
አርትስ ቲቪ ፕሬዚዳንት ሣህል ወርቅ ዘውዴ ይሄ ጦርነት የእርስበርስ ጦርነት ነው በማለት ለፈረንሳይ መጽሔት ገልፃለች የሚለውን የፌስቡክ ልጥፍ ተመልክቶ ሐሰተኛ ሆኖ አግኝቶታል፡፡
. . . . .
ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::
እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::
በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::
ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ ም/አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::
አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ ዋ/አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::
ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::
ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::