loading
ሀምዶክ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጀምረዋል፡፡

ሀምዶክ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጀምረዋል፡፡

አዲሱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ወደ ጁባ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከሩ ነው፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ወደ ደቡብ ሱዳን የተጓዙት፡፡

በውይይቱ ወቅት ከሱዳኗ አቻቸው አሳም አብደላ ጋር ሆነው መግለጫ የሰጡት የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አውት ዴንግ አኩይል በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ቅራኔ  ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡

ሀምዶክ ጁባ እንደደረሱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከጎረቤት ደበቡብ ሱዳን ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር የትኛውንም ስልት እንከተላለን ብለዋል፡፡

ካርቱም እና ጁባ በንግድ፣ በድንበር አካባቢ ያሉ ክርክሮችን በማስወገድ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርበው እንዲሰሩ ምክክር መጀመራቸውንም  ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *