loading
የዘንድሮው የሻደይ በዓል ከነሐሴ 16 እስከ 18 በዋግኸምራ ብሔረሰብ ዞን” ሻዴይ በዓላችን ለገጽታ ግንባታችን” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል፡፡

የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ተክሉ ለአርትስ እንደገለጹት በዓሉ በሁሉም ወረዳዎች በጎዳና ላይ ትርኢቶች እና ባህላዊ ክዋኔዎች ይከበራል ፡፡ ከበዓሉ አከባበር ጎን ለጎን በሰቆጣ ከተማ የባህል ሲምፖዚየም የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በዓሉን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ […]

ኢትዮጵያ ከቱሪስቶች 3. 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር አገኝች፡፡

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት በ2010 ዓ.ም ኢትዮጵያን ከጎበኙ 934 ሺ ቱሪስቶች 3.5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ ከጎብኝዎች መካከል የቻይና ቱሪስቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ሲሆን፤ የእንግሊዝ እና የአሜሪካን ዜግነት ያላቸዉ ቱሪስቶችም በብዛት ሀገራችንን ጎብኝተዋል፡፡ ለገቢዉ መገኘት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከባለድርሻ አካላትጋር ዘርፉን ለማሳደግ በጋራ መስራቱና የኢትዮጵያ […]

የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘቱን መቀየሩ አሳስቦኛል አለ::

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ፡፡ በባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የጋራ ባህል እሴትዳይሬክተር አቶ አለማየው ጌታቸው የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘት እየተቀየረ መምጣቱንና ስነቃሎቹም ላይ ጥናት ሊደረግ መሆኑን ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ባህል እና ቱሪዝም ቡሄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማደረጉን ገልፀው በመጪው ቡሄ ስነቃላዊ ጥናቶችን ለማድርግ በፌደራል ደረጃ መስሪያ ቤቱ […]

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንድነት ላይ ያተኮሩ በዓላትን ላዘጋጅ ነዉ አለ፡፡

ከነሐሴ አጋማሽ አስከ መስከረም 30 የሚቆየዉ የበዓላት ዝግጅት “አንድ ሆነን አንድ እንበል” በሚል መሪቃል የሚከበር ነዉ፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሚዘጋጁት የተለያዩ በዓላት ለአዲስ አመት የሚመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ቱሪስቶችን መቀበል ላይ ያተኮረ ነዉ ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ በሆቴሎች በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በአስጎብኚ ድርጅቶች ያገልግሎት ዋጋ ቅነሳ በተጨማሪ ሁላችንም ኢትዮጵያዉን ፤ኢትዮጵያዊ በሆነ […]

በአንዳንድ አካባቢዎች እየተፈጠረ ያለው አለመረጋጋት የቱሪዝም ዘርፉ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ተባለ፡፡

ይህ የተባለው የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ትላንት በመስሪያቤቱ በሰጠው መግለጫላይ ነው፡፤ በመግለጫው የቱሪዝም ዘርፍ ሰላም እና መረጋጋትን የሚሻ ዘርፍ እንደመሆኑ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተከሰቱት ግጭቶች ቱሪስቶችን እና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን ዲያስፖራዎችን የሚያሸሽ ነው ተብሏል፡፡ በባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ድርጊት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንደሚያወግዘው ገልፀው ለሰላም እና መረጋጋት […]

የዘንድሮው የአሸንዳ በአል በመቀሌ ከተማ ስታዲየም “አሸንዳ ለሰላም እና አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል፡፡

በክብረ በዓሉ የመንግስተ አመራሮች፣ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸአው ታዳሚዎች ተገኘተውበታል፡ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሶፊያ አሚን የህዝቦች አንድነት፣መፈቃቀር፣አብሮ የመኖር ትስስርን ከሚያጠናክሩ ጠቃሚ እሴቶች እና ክብረ በአላት መሃከል አሸንዳ አንዱ እንደሆነ ገልፀው እነዚህ እሴቶች የሰላም እና አንድነት ማገር ሆነው ከትውልድ ትውልድ ይተላለፉ ዘንድ ጠንክረን መስራት አለብን ብለዋል፡፡ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደ/ር […]

ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ በላሊላ አሸንድዬ ካባ ተደረበላቸው።

አሸንድዬ፣አሸንዳ ፣ሶለል እና ሻደይ የዓለም ሀብት የሚሆኑት በባለቤትነት ስንጠብቃቸው ነው ብለዋል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን። የአሸንድዬ የሴቶች በዓል “አሸንድዬ ለሰላምና አንድነት በፍቅር ለመደመር” በሚል መሪ ቃል በላሊበላ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ ወጣቶች ለሰላም ስሩ ሲሉ ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ደግሞ ባህል የሚታወቀው አገር ሲኖር ነው ብለዋል ። አርትስ ቲቪ […]

የ 2010 የአሸንዳ በዓል ብዛት ያለዉ ቱሪስት የተገኘበት ነዉ ተባለ፡፡

አርትስ 18/12/2010 የዘንድሮዉ የአሸንዳ በዓል ከማነኛዉም ግዜ በበለጠ ከመላዉ አለም የመጡ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን በስፋት የተሳተፉበትና ብዛት ያላቸዉ ኤርትራዊያን የተገኙበት መሆኑን የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  ለአርትስ ቲቪ ገልጸዋል፡፤ የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከፍተኛ የቱሪስት ፍሰት ስለነበርም ግብይቱ እንደተነቃቃ ነግረዉናል፡፡ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ አልባሳት ሽያጭም ከፍተኛ እንደነበር ሰምተናል፡፡ከተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎችም የመጡ የተለያዩ ብሄር […]