ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዘዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዘዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ::
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዘዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ::
የህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘዉ በቀለ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመኪናቸዉ ዉስጥ ሞተዉ ተገኙ፡፡
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ አገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር አብይ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ከሚያራምዱ ኢትዮጵያውያን የፓርቲ መሪዎች ጋር የሚነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሜሪካ […]
የኢንጀነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነ – ሥርዓትን እሁድ ሀምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ይፈጸማል ፡፡ ብሔራዊ የቀብር አስፈሚ ዐብይ ኮሚቴ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ የቀብር ሥነ-ስርአቱ ዕሁድ ሐምሌ 22 ቀን 2010. ከቀኑ 7፡00 ሰአት በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ በሚገኘው በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ የሥራ ባልደረቦች እና መላው ህዝብ በተገኙበት […]
ዛሬ በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ የአራት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን በመደገፍ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የተደረገው ሰልፍ ላይ ከፈነዳው ቦምብ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ላይ ፍ/ቤቱ የተጠየቀውን ጊዜ ቀጠሮ ተቀብሏል፡፡
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የሚያደርጉትን ንግግር ተከትሎ ዕለቱ የኢትዮጵያውያን ቀን ተብሎ እንዲታሰብ ተወስኗል።
ከሃላፊነታቸው የተነሱት የቂሊንጦ ፤ የቃሊቲ፤ የሸዋ ሮቢት እና የድሬዳዋ ማረሚያቤቶች አስተዳዳሪዎች መሆናቸዉን አርትስ ቲቪ ለማወቅ ችሏል፡፡ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረዳት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ለ አርትስ እንደለፁት፤ በቅርቡ ታራሚዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ የሠብዓዊ መብት ጥሠት እንደሚፈፀምባቸው በመናገራቸዉ እና ማረሚያ ቤቱም አስተዳዳሪዎቹ ጋር ችግር እንዳለ በማረጋገጡ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ […]
ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል የተስማሙት ከ15 አመታት በኋላ መሆኑን ኤርቲሪያን ፕረስ ዘግቧል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዘዳንት መሃመድ ፋርማጆን ኤምባሲያቸውን ለመክፈትና አምባሳደር ለመሾም ተስማምተዋል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ቀጠናዊ ግንኙነትን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዘዳንት መሃመድ ፋርማጆን በበኩላቸው በሁለቱም ሃገራት ዋና ከተሞች በቅርቡ ኢምባሲዎቻችንን ጠብቁ ብለዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአሜሪካ ጉዞ ግንቡን በማፍረስ ድልድዩን በመገንባት ተጠናቀቀ ፡፡