loading
ሰባት ኪሎ ወርቅና በርካታ ዶላር በኮንትሮባንድ ሊገባ ሲል ተያዘ

ክብደቱ ሰባት ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የዉጭ ሃገር ገንዘብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። ይኸው ወርቅና ገንዘብ የተያዘው በቶጎ ዉጫሌ ኬላ ላይ በሚሰሩ የጉምሩክ ሰራተኞች ሲሆን በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ኮንትሮባንድ ነጋዴዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሚኒስቴሩ የተያዘውን ገንዘብ መጠን  ቆጠራው ካለቀ በኋላ አሳውቃለሁ ብሏል።

ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም አዋጅ አፀደቀች፡፡

ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም አዋጅ አፀደቀች፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ ስብሰባው የጦር መሳሪያ  አስተዳደር አዋጅ አፅድቋል፡፡ የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ  መስፍን ቸርነት የአገርና የህዝብን  ፀጥታ እና ሰላም ለማስጠበቅ ያለመ ነው ብለዋል፡፡ ግለሰቦች የታጠቋቸውን መሳሪዎች የሕብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ተግባር ላይ እንዲያውሉ እንዲሁም ህገ-ወጥ የጦር መሳሪዎች ዝውውርን […]