loading
ከስድስት ወራት በኋላ የሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ዶክተር አብይ ይህንን ያሉት በባህርዳር ከተማ ከብአዴን አመራሮች ጋር ባደረጉት ምክክር ላይ ነው፡፡ ባለፉት 9 ወራት የተሻለ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለማምጣት ውጤታማ ተግባራት ተከናዉነዋል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የተሻለ መግባባት ለመፍጠርም ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የነበረውን ግንኙነት የማስተካከልና በሀይማኖቶች ውስጥ የነበረውን መከፋፈል የማጥፋት ስኬታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በኢኮኖሚ ረገድም የውጭ ምንዛሬ በቤታቸው ያከማቹ ዜጐች ወደ ባንክ […]

ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ አደረገ፡፡ 

በዚህም መሰረት የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የ43 ከመቶ፣ የብሮድባንድ ኢንተርኔት ላይ የ54 ከመቶ፣ የስልክ ድምፅ ላይ የ40 ከመቶ እንዲሁም የሞባይል የፅሁፍ መልዕክት (SMS) ላይ የ43 ከመቶ ቅናሽ ማድረጉን ሰምተናል፡፡ መረጃውን ሸገር የሰማሁት ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ነው ብሎ በድረ ገፁ አስነብቧል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኮየ ፈጬ ሳይት የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበትን ደረጃ ጎበኙ

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራውና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልኡካን በ11ኛው ዙር የተላለፉ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል። ነዋሪዎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ባለማሟላቱ ቅሬታቸውን ገልጸውላቸዋል በተለይም የውሃ፣ የመብራት  እና የባለድርሻ አካላት በቅንጅት ተናበው አለመስራት በኑሮአቸው ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ነው የገለጹት፡፡ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለም የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች የህብረተሰቡን ቅሬታ ወስደው […]

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተፈቅዶላታል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዳሉት ድጋፉ በቀጥታ የሀገሪቱን በጀት የሚደግፍ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዓለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት  በ97 በኢትዮጵያ በተካሄደው ምርጫ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ለቀጥታ በጀት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርገው አያውቁም፡፡ ለገንዘቡ መገኘት አሁን በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ዋኛው ምክንያት መሆኑንም ዶክተር አብይ ተናግረዋል፡፡ የዓለም ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ጂም ያንግ ኪም በበኩላቸው […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጥቅምት ወር መጨረሻ ለይ ጀርመን ሊጓዙ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከጀርመኗ ቻንስለር መራሂተ መንግስት ወይዘሮ አንግላ መርከል ጋር በስልክ አውርተዋል፡፡ የጠቅለይ ሚንስቴር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በገፃቸው እንዳስነበቡት ቻንስለር መርከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጭር ጊዜ እያካሄዱ ላሉት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራዎች በተለይም ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም አድናቆታቸውን በመግለጽ እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋቸዋል፡፡ ቻንስለሯም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀርመን ተገኝተው […]

የመንግስት ባለስልጣናት ቪ8 ተሽከርካሪዎችን ከተማ ውስጥ እንዳይጠቀሙ የሚከለክለው መመሪያ በቀጣዩ ሳምንት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል

  ኤፍ.ቢ.ሲ  እንደዘገበዉ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የሌሎች ተቋማት ሀላፊዎች ቪ8 ተሽከርካሪዎችን ከተማ ውስጥ እንዳይጠቀሙ የሚከለክለው መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው። መመሪያው ባለስልጣናቱ እና የስራ ሀላፊዎቹ ከዚህ ቀደም በከተማ እንቅስቃሴ ወቅት ይጠቀሙባቸው የነበሩ ቪ8 ተሽከርካሪዎችን ለመስክ ስራ ብቻ እንዲጠቀሙ የሚደነግግ መሆኑንም የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሐጂ ኢብሳ በሰጡት መግለጫ፥ […]