loading
አሁን የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሶስትዮሽ ጉባኤ በአቡ ዳቢ እየተካሄደ ነዉ

በዚህ የሶስትዮሽ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በሶስትዮሽ ውይይት ላይ የሶስቱ ሀገራት የኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰሩ ሆቴሎች ባህልን የሚያንፀባርቅ ገፅታ ሊኖራቸዉ ይገባል ተባለ

ይህ የተባለዉ የካፒታል ኢንተርናሽናል ሆቴል የባህል አዳራሹን ሲያስመርቅ ነው፡፡ በካፒታል ሆቴል የባህል አደራሽ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ የተገኙ ሲሆን ምክትል ከንቲባዋ ዳግማዊትም ከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ባህል አዳራሾች ያስፈልጓታል ፤በባህል ላይ የሚሰሩ ባለሀብቶችንም እናበረታታለን ብለዋል፡፡ የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስአለም ገብሬ በሆቴላቸዉ ዉስጥ ልዩ […]

በገበሬዎችና በእንስሳት አርቢዎች መካከል ነፍስ መጠፋፋት ለናይጀሪያ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡

በገበሬዎችና በእንስሳት አርቢዎች መካከል ነፍስ መጠፋፋት ለናይጀሪያ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡ ፕሬዝዳንት ማማዱ ቡሀሪ ሀገራቸውን ሰላም ከነሳት ነገር የመጀመሪያው የቦኮሀራም ጥቃት ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በተደረገ ጥናት ሌላ አስደንጋጭ ክስተት መፈጠሩን የሚያሳይ መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በዚህ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በከብት አርቢዎችና በአርሶ አደሮች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከ1ሽህ […]

ኤርትራና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል ተስማሙ ፡፡

ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል የተስማሙት ከ15 አመታት በኋላ መሆኑን ኤርቲሪያን ፕረስ ዘግቧል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዘዳንት መሃመድ ፋርማጆን ኤምባሲያቸውን ለመክፈትና አምባሳደር ለመሾም ተስማምተዋል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ቀጠናዊ ግንኙነትን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዘዳንት መሃመድ ፋርማጆን በበኩላቸው በሁለቱም ሃገራት ዋና ከተሞች በቅርቡ ኢምባሲዎቻችንን ጠብቁ ብለዋል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ጉዳይ ላይ መክሯል፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ለቀረበላት የእርቅ ጥያቄ የሰጠቸው አወንታዊ ምላሽ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ታዲያ ለዚህ የሰላም አጋዥነቷ የተጣለባት ማእቀብ እንዲነሳላት ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታ ድርጅት ጥያቄ አቅርባ ነበር፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው አሁን ላይ ድርጅቱ የኤርትራ ማእቀብ ይነሳ ወይም አይነሳ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስዊድን አምባሳደር ኦልፍ ስኩግ እንዳሉት ኤርትራና […]

ግብጻዊው ጸሀፊ ግብጽ ወደ ንጉሳዊ የአገዛዝ ዘመን እንድትመለስ ጥያቄ አቀረበ፡፡

ዳንድራዊ አል ሀዋሪ የተባለው ግብጻዊ ደራሲ ሀገሪቱ ወደ ቀድሞው ስርዓት ስትመለስ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ደግሞ ንጉስ ሆነው መሰየም አለባቸው የሚል ሃሳብም አቅርቧል፡፡ የደራሲውን ሀሳብ ብዙዎች አውግዘውታል፣ በርካቶችንም ለብስጭት ዳርጓል ይላል የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ፡፡ ከአስተያየት ሰጭዎቹ መካክል እንዲህ አይነቱ ሀሳብ ግብዝነት የተሞላበትና ሀገሪቱን የማይጠቅም ነው በማለትም አጣጥለውታል፡፡

ዛኑፒኤፍ አብላጫውን የፓርላማ መቀመጫ አሸንፏል ተብሏል፡

በዚምባቡዌ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ ዛኑ ፒ ኤፍ አብላጫ የፓርላማ ወንበር ማሸነፉ ይፋ ሆኗል፡፡ ሮይተርስና አልጀዚራ ከሀራሬ የሀገሪቱን የምርጫ ኮሚሽን ጠቅሰው እንደዘገቡት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የሚመሩት ዛኑ ፒፍ ፓርቲ 109 መቀመጫዎችን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ የተሰኘው ተቃዋሚ ፓርቲ ደግሞ 41 መቀመጫዎችን አሸንፏል ነው የተባለው፡፡ ቀሪዎቹን 58 መቀመጫዎች ማን እንዳሸነፈ ገና ያልተገለጸ ሲሆን […]

እንግሊዝ የዚምባቡዌ ነገር አሳስቦኛል ብላለች፡፡

አሁንም በአፍሪካ ምድር በምርጫ ማግስት ሰው ይገደላል፡፡ በዚምባቡዌ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤቱ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡ የፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነው በምርጫው የቀረቡት ኔልሰን ቻሚሳ የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ አሸናፊ ሆኗል መባሉን ባለመቀበላቸው ደጋፊዎቻቸው ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የምናንጋግዋ ወታደሮችም ሰልፈኞቹ ላይ ተኩሰዋል፡፡ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸው ታወቋል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ መገናኛ ብዙሀን ቁጥሩን […]