loading
በጊኒ ምርጫ ማግስት በተቀሰቀሰ ግጭት አስር ሰዎቸ መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 በጊኒ ምርጫ ማግስት በተቀሰቀሰ ግጭት አስር ሰዎቸ መገደላቸው ተሰማ:: የአፍሪካ ህብረትና የምእራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ ሂደቱ ሰላማዊ ነበር ብለው :: የመሰከሩለት የጊኒ ምርጫ ውጤቱ ገና በይፋ ሳይገለፅ ብጥብጥ አስከትሏል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው የተቃዋሚ መሪው ሴሎ ዲያሎ ገና ድምፅ ቆጠራው ሳይጠናቀቅ አሸንፌያለሁ ብለው ለደጋፊዎቻቸው ከተናገሩ ከቀናት በኋላ ጊዜያዊ ውጤቱ ፕሬዚዳንት አልፋ […]

በኮቪድ 19 ምክንያት በአፍሪካ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 40 ሺ አለፈ:

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 በኮቪድ 19 ምክንያት በአፍሪካ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 40 ሺ አለፈ:: የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ ባደረገዉ መረጃ ደቡብ አፍሪካ ከ18 ሺ 656 በላይ ዜጎቿን በኮቪድ 19 ምክንያት በማጣት በአሁጉሪቱ ቀዳሚ ሀገር ናት፡፡ አሁን ላይ በአፍሪካ አህጉር በአጠቃላይ በወረርሽኙ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ40 ሺ አልፏል፡፡ 6 ሺህ አንድ መቶ አርባ […]

በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ::በከተሞች ለሰላም እጦት መንስኤ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ፡፡ ፕሬዝዳንቷ ይህን ያስታወቁት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች የሰላም ፎረም ላይ ነው፡፡”የፍትህና ተጠያቂነት መጓደል፣ የኑሮ ደረጃ ልዩነቶች፣ እንዲሁም ስራ አጥነት በከተሞች የሚስተዋሉ […]

የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር የሚዘልቅ ነው ሲሉ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013የአገር መከላከያ ሠራዊቱ ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር የሚዘልቅ ነው ሲሉ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ገለፁ:: እየተገነባ ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከፖለቲካው ጋር የሚወድቅ የሚነሳ ሳይሆን ከአገርና ከሕዝብ ጋር ዘላቂነት ያለው ነው” ሲሉ በሠራዊቱ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሹማ አብደታ ተናገሩ።ሜጄር ጄኔራሉ ሠራዊቱ በሰው ኃይል […]

ለትግራይ ወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሰራር ዝግጅት ማጠናቀቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 ለትግራይ ወረዳ፣ ከተማና ቀበሌ የድጎማ በጀት የሚተላለፍበት አሰራር ዝግጅት ማጠናቀቁን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃጂ ኢብሳ እንደተናገሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ሚኒስቴሩ ለክልሉ ወረዳዎች ፣ ከተሞችና ቀበሌዎች የድጎማ በጀቱን የሚያስተላልፍበትን የአሰራር ዝግጅት አጠናቋል፡፡በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው የበጀት ድጎማ አሰራር በሚቀጥለው ሳምንት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ […]

የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሰረተ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሰረተ::የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ምስረታ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ተደረገ። በማህበሩ ምስረታ ላይም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ […]

በአየር ብክለት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ህፃናት ህይዎታቸው ማለፉን አንድ ጥናት አመለከተ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013በፈረንጆቹ 2019 በአየር ብክለት ምክንያት ከ400 ሺህ በላይ ህፃናት ህይዎታቸው ማለፉን አንድ ጥናት አመለከተ::ሄልዝ ኢፌክት ኢንስቱትዩት የተባለ ተቋም እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2019 በዓለማችን 476 ሺህ ጨቅላ ህፃናት የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ችግር ሳቢያ ህይዎታቸው ማለፉን በጥናት አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ከነዚህ የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ህፃናት መካከል አብዛኞቹ ከህንድና ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው […]

በፈረንሳይ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በአንድ ሳምንት ውስጥ በ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 በፈረንሳይ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በአንድ ሳምንት ውስጥ በ40 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተባለ::በመላው አውሮፓ እንደ አዲስ እየተስፋፋ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ፈረንሳይንም ከፍተኛ ስጋት ለይ ጥሏታል፡፡ የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂያን ካንቴክስ በሰጡት መግለጫ ችግሩ በጠቅላላው አውሮፓም በሀገራችንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡የወረርሽኙ ስርጭት ያሳሰባት ፈረንሳይ በተመረጡ አካባቢዎች የሰአት እላፊ ገደቦችን ለመጣል ተገዳለች፡፡ዩሮ […]

ስፔን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ደነገገች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 ስፔን የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የሰዓት እላፊ ገደቦችን ደነገገች::የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቸዝ ለመነሻነት ለ15 ቀናት የተጣለው ድንጋጌ ለስድት ወራት እንዲራዘም ፓርላማቸዉን እንደሚጠይቁ ተናግረዋል፡፡በተለያዩ ግዛቶች የተጣሉት የምሽት ጊዜ የሰዓት እላፊ ገደቦች እንደአስፈላጊነቱ ሊያጥሩና ሊረዝሙ አንደሚችሉ ነው የተነገረው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው አዲሱ የስፔን የእንቅስቃሴ እቀባ በግልም ሆነ በመንግስት […]

የጤናውን ዘርፍ ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የግሉ ዘርፍ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 የጤናውን ዘርፍ ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ የግሉ ዘርፍ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ::የጤና ጥበቃ ሚንስተር ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለጤናው ዘርፍ መንግስት ከሰጠው ትኩረት ጎን ለጎን የግሉ ዘርፍ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። ዶክተር እመቤት ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ አሁን ላይ በአለማችን የጥርስ ህክምና የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆነውን ካድ ካም […]