loading
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንድሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወርቅ ሜዳልያ ያገኙ ተመራቂ ተማሪዎችን ሊያነጋግሩ ነዉ ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንድሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወርቅ ሜዳልያ ያገኙ ተመራቂ ተማሪዎችን ሊያነጋግሩ ነዉ ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀዉ የዘንድሮ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተማሪዎች የሚሳተፉበት ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
ዝግጅቱም ከሐምሌ 16 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ይቆያል፡፡

በዝግጅቱ ላይም ከሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች የተውጣጡ 400 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች መጋበዛቸውን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል ።

በዝግጅቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተገኝተው ከተመራቂ ተማሪዎቹ ጋር የውይይት ጊዜ እንደሞኖራቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹ ከውይይቱ በኋላም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን እና የቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትንና መስሪያ ቤቶችን ይጎበኛሉ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *