loading
የዘንድሮ የኢ.ቢ.ሲ የስፖርት ሽልማት በመጪው መስከረም በሸራተን አዲስ እንደሚደረግ ይፋ ሆነ፡፡

በ 2009. ዓ.ም የተጀመረው የኢ.ቢ.ሲ የአመቱ ምርጥ የስፖርት ሽልማት በዘንድሮ አመትም ለሁለተኛ ጊዜ በአምስት ዘርፎች እንደሚያካሄድ ኮርፖሬሽኑ አስታዉቋል፡፡
የኢ.ቢ.ሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አቤል አዳሙ ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ጋር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት በእግር ኳስ ዘርፍ እና በአትሌትክስ ዘርፍ በሁለቱም ፆታዎች ፤ከአምናው በተለየ ደግሞ የህይወት ዘመን ተሸላሚ ዘርፍም በዘንድሮዉ ሽልማት ተካቷል፡፡
እነዚህን እጩዎች ለመለየት በፁሁፍ መልዕክት 800 ላይ አድማጭ ተመልካችን በማሳተፍ 30 በመቶ ድምፅ እንዲይዝም ተደርጓል፡፡ቀሪው የስፖርት ቤተስብ እና ባለሙያዎች 70 በመቶውን ድምፅ ይይዛል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *